የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ኅብረት ከሦስት ሺሕ በላይ የምርጫ ታዛቢዎችን ለማሰማራት ተዘጋጀ

0
627

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ሕብረት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከ3 ሺህ በላይ የምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚያሰማራ አስታወቀ።
በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ 170 የሲቪል ማህበራትን ያቀፈው “የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ህብረት ለምርጫ” የተሰኘው ጥምረት አስተባባሪ አቶ አበራ ኃይለማርያም በዚህ ወቅት ለመገናኛ ብዙኀን እንዳሉት፤ ህብረቱ በግንቦት ወር የሚካሄደውን አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ ተዘጋጅቷል።
በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት አዘጋጅነት የሲቪክ ማህበራትና የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ተወካዮች የታደሙበት “ምርጫና ሰብዓዊ መብት” የተሰኘ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በዚህም በአገሪቱ 83 ዞኖችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በቅድመና ድህረ ምርጫ እንዲሁም በምርጫው ዕለት ታዛቢዎቹን እንደሚያሰማራ ነው የተናገሩት።
ከነዚህም መካከል በቅድመ ምርጫ 250፣ በምርጫ ወቅት ደግሞ 1 ሺህ 250 ተቀማጭና 500 ተንቀሳቃሽ የምርጫ ታዛቢዎች ይሰማራሉ።
የሲቪክ ማህበራት በምርጫ ወቅት የሚኖራቸው ሚና ከምርጫው በፊት፣ በምርጫ ዕለትና በድሕረ ምርጫ የሚኖሩ ቅሬታና አለመግባባቶች እንዲፈቱ ከ250 በላይ ታዛቢዎችን ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ማህበራቱ ከታዛቢነት ባለፈም በምርጫ ትምህርትና ክትትል ላይ እንደሚሰራ አስተባባሪው ገልጸዋል።
ከምርጫው በፊት በአምስት ቋንቋዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ትምህርት ለመስጠት እንደተዘጋጀም አስሠታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 120 የካቲት 13 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here