የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ስር በሚገኘው የአየር ወለድ ትምህርት ቤት አዲስ ህንጻ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ በቢሸፍቱ አየር ኃይል ጊቢ አስቀምጠዋል።
የሚገነባው ሕንጻ የትምህርት ቤቱን አቅም ለማጠናከር የሚያገለግል መሆኑ ታውቋል።
ሕንጻው በ170 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባ ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ተሰርቶ እንደሚጠናቀቅም ተነግሯል።
ከዚህ በተጨማሪም አጠቃላይ የአየር ወለድ የስልጠና ሂደት ጉብኝት ተደርጓል። የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይና የተኩስ ትርኢት አካሒዷል።
ከተቋቋመ 60 ዓመታትን ያስቆጠረው አየር ወለዱ አዲሱ የሕንጻ ግንባታ ዘመናዊ የመሰረተ ልማት እንዲኖረው ያስችላል ተብሏል።
ቅጽ 2 ቁጥር 122 የካቲት 27 2013



