ፍርድ ቤቱ ስለ ‹‹መርዙ›› መስማት አልፈልግም አለ

0
510

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጅል ችሎት ጉዳያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙትና በእነጎህ አጽብሃ መዝገብ ተጠርጥረው የተያዙት 33 የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንየተያዙ ግለሰቦችስለ መርዙ እናስረዳ ቢሉም ፍርድ ቤቱ መስማት አልፈልግም አለ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ቢሮ ውስጥ ተገኘ በተባለው ‹‹መርዝ ስማችን እየጠፋ ነው ባላደረግነው ወንጀልም እየተከሰስን ነው›› በሚል ‹‹የመርዙን ምስጢር ለመናገር እንፈልጋለን›› ቢሉም ፍርድ ቤቱ ለመስማት ፍቃደኛ ባለመሆኑ በዚህ ላይ ሐሳባቸው ሳይሰማ ቀርቷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ባልፈጸሙት ወንጀል ስማቸው እየጠፋ መሆኑን ለችሎቱ በመጥቀስ ‹‹የመርዙን ምስጢርእናወጣልን›› ቢሉም ፍርድቤቱ ምስጢራቸውን የመስማት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል፡፡
በእነጎህ አጽብሃ መዝገብ ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር የሚገኙት 33 ግለሰቦች ይህን ያሉት ረቡዕ ጥር 1/2011 በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጅል ችሎት በቀረቡበት ወቅት ነው፡፡
ስለሚባለው መርዝ ምስጢሩን እንደሚያወጡ ለችሎቱ ተናግረው እንዲገልጹ ላልተፈቀደላቸው ተጠርጣሪዎች ምላሽ የሰጠው ችሎቱ፣ የተሰየመው የጊዜ ቀጠሮን ለመስማት እንደሆነ አስታወቆ ወደፊት ከክስ በኋላ በሚደረጉ ክርክሮች ጉዳዩን ማቅረብ እንደሚችሉተናግሯል፡፡
በዕለቱም ለችሎቱ በርካታ አቤቱታዎች በተጠርጣሪዎች በኩል የተነሱ ሲሆን ‹‹ከጠበቆቻችን ጋር እንድንገናኝ እየተደረገ አይደለም፣ፖሊስ ሁልጊዜም ተመሳሳይ መረጃ ነው የሚያቀርበው፣ የዋስ መብታችንም ሊጠበቅልን ይገባል›› የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ‹‹አሁን ላይ የተያዘው ወንጀል መመርመር ሳይሆን ወንጀል መፍጠር ነው›› የሚሉ መከራከሪያዎችንም ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ‹‹የሰራነው ሥራም መንግሥትን በመታዝዘ የፈጸምነውእንጂበግላችን ያደረግነው ምንም ነገር የለም›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ የዋስ መብት ቢሰጣቸው ምስክሮችን ሊያስፈራሩብኝ ይችላሉ በሚል የዋስትና መብት ጥያቄው ተቀባይ እንዳይሆን አመልክቷል፡፡
ተጠርጣሪዎች በበኩላችው ፖሊስ ያነሳውን ሐሳብ በመቃወም ‹‹ምስክሮችን ልንፈራ የምንችለው እኛ ነን፤ ምስክሮቹ እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠንቅቀን እናወቃለን›› ሲሉምምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የተጠርጣሪዎችንና መርማሪ ፖሊስን ሐሳብ ያደመጠው ፍርድ ቤቱ በማግስቱ ሐሙስ ቀጠሮሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በተባለው ዕለት የእነሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኛውን ጉዳይ ለመመልት ችሎት በመቀመጡ ይህ ጋዜጣ ለኅትመት እስከገባበት ትናንት ምሽት ድረስ ተለዋጭ ቀጠሮው ለመቼ እንደተባለ የታወቀ ነገር የለም፡፡
በመንግሥት ከወራት በፊት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረውበቁጥጥር ስር የዋሉትየአዲስ አበባ የጸጥታ ጉዳዮች ኃላፊ ጎሃ አጽብሃን ጨምሮ 33 ተከሳሾች ጉዳያቸውን ማረሚያ ቤት ሆነው እየተከታተሉ ነው፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 9 ጥር 4 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here