በዓለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ለተፈጠረው ቀውስ ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ዓለም አቀፋዊ አንድነት እንደሚያስፈልግ ደመቀ መኮንን ተናገሩ

0
606

በዓለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ለተፈጠረው ቀውስ ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ዓለም አቀፋዊ አንድነት እንደሚያስፈልግ ደመቀ መኮንን ተናገሩ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት ያለመ የሁለት ቀናት የቪዲዮ ኮንፈረንስ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ደመቀ በመልዕክታቸውም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ለተፈጠረው ቀውስ ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ዓለም አቀፋዊ አንድነት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በተጨማሪም እየታየ ላለው የኮቪድ 19 ክትባት አበረታች እድገት እና ተነሳሽነት ኢትዮጵያ ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።ለዚህ ስኬት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል ።
ከዚህ ባለፈም ክትባቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለህዝብ ጥቅም እንዲውልና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለሁሉም ተደራሽ መሆን አለበት የሚለውን ዓለም አቀፍ መግባባት ኢትዮጵያ ትደግፋለች ነው ያሉት።
ወረርሽኙ ባስከተለው ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ አፍሪካ የቡድን 20 ሃገራት እዳን በማቃለል እና የእፎይታ ጊዜን በመስጠት ውጤታማ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ፓኬጅ እንዲያቀርቡ ጥሪ ማቅረቧን አስታውሰዋል።
በተጨማሪም ከዚህ ስብሰባ የተባበረ ዓለም አቀፋዊ ምላሽን የሚያነቃቃ እና የሚያስተባብር እንዲሁም ሁሉን አቀፍ፣ ዘላቂ፣ አረንጓዴ እና የማይበገር ሁኔታን ለመፍጠር የሚያስችል እንደሚሆን ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘነው መረጃ ያመላክታል።


ቅጽ 3 ቁጥር 127 ሚያዚያ 2 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here