ዳሸን ባንክ ዓለም ዓቀፍ ክፍያን ለማከናወን የሚያስችል የበይነ መረብ ንግድ ማቀላጠፊያ መስመር አስመረቀ

0
961

ዳሸን ባንክ ዓለም ዓቀፍ የ‹‹ቪዛ ሳይበርሶርስ›› መሰረተ ልማትን በመጠቀም በአሞሌ ቴክኖሎጂ ከሶስት ዓለምአቀፍ የመገበያያ ካርዶች ጋር በመሆን ዓለም ዓቀፍ የበይነ መረብ ንግድ ማቀላጠፊያ መስመር አስጀመረ።
ከ2018 ጀምሮ አሞሌ በተሰኘው ቴክኖሎጂ የ‹‹ኢ- ኮሜርስ›› ክፍያ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው ዳሸን ባንክ፣ በዋናዎቹ ዓለም ዓቀፍ የግብይት ካርዶች ማለትም ቪዛ ካርድ፣ ማስተር ካርድና አሜሪካን ኤክስፕረስ አማካይነት 8 ሺህ የንግድ ማእከላትን የድህረ- ገጽ ንግድ ማከናወን እንዲችሉ በማድረግ የመጀመሪያው ባንክ መሆኑንም አስታውቋል።

ባንኩ ከቪዛ አለም አቀፍ ማህበር ጋር ግንኙነት የጀመረው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2005 የመጀመሪያውን የፕላስቲክ ካርድ፣አውቶማቲክ የመክፍያ ማሽን እና የክፍያ ተርሚናሎችን ካስተዋወቀበት ጊዜ ጀምሮ እንደነበር የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አስፋው አለሙ አስታውሰዋል።

በሌለ አዲስ ምእራፍ ደግሞ ትብብር አንደሚያስፈልግ በማመን ከ‹‹ሞኔታ ቴክኖሎጂሰ›› ጋር በ2018 ግንኙነት ፈጥሮ የክፍያ ስርዓትን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሚያሳልጥ ስርዓት በአሞሌ የክፍያ ስርዓት እየሰሩ መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል።
አሁን ላይ የቪዛ ሳይበር ሶርሲንግን በመጠቀም በአሞሌ የኤሌክትሮኒክስ መገበየያ መግቢያ በር ወይም ጌት ዌይ የዓለም አቀፍ ክፍያዎችን ለመቀበል የሚያስችል በር መከፈቱን አብስረዋል።

ይህ ሥርዕት በሶስቱም ካርዶች፣ በሁሉም የዓለማችን ክፍል ግብይት ማከናወን መቻሉ እና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ የዓለም አቀፍ ካርድ ማህበራቱ ማረጋገጣቸውን ዋና ሥር አስፈጻሚው ተናግረዋል።
ሁሉንም ምርት እና አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ማስቻሉ ለሸማቾች ጊዜ ከመቆጠቡ ባለፈ የተሟላ መረጃ እንዲያገኙ ማስቻሉ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ አንስተዋል።

አበበ ግርማይ፣ የቪዛ ካርድ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር፣ ዳሸን ባንክ በቪዛ ካርድ እና በሞኔታ ቴክኒሎጂ አማካይነት ያቀረበው የአሞሌ የክፍያ ስርዓት የዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን ተጠቅሞ ዓለም አቀፍ ንግድ ለማቀላጠፍ ይረዳል ብለዋል።
የዲጂታል ክፍያ ስርዓትን በማቀላጠፍ እና የፋይናንስ ስርዓት አካታችነትን በማሳደግ ቪዛ ካርድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፣ ባንኩ መንግስት ጨምሮ ፣ከባንኮች፣ ከንግድ ተቋማት እንዲሁም ከነጋዴዎች ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነት እንዳለው አበበ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ ተቋማት፣ በድረ ገጽና በሞባይል መተግበሪያዎች ዲጂታል ክፍያን መቀበል የሚችሉበት ሁኔታ እስካሁን አልተፈጠረም የሚለው የዳሸን ባንክ መረጃ፣ በዚህም ምክንያት ሆቴሎች፣ አስጎብኚ ድርጅቶችና የምርት አከፋፋዮች ለዓለም አቀፍ ደንበኞቻቸው ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን ለመሸጥ ሳይችሉ ቆይተዋል ብሏል።

በተለይ ሆቴሎች ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን በመቀበል ደንበኞች ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ቀድመው መኝታና ተያያዥ አገልግሎቶችን እንዲይዙ የሚያደርጉበት አማራጭ ያልነበራቸው በመሆኑ፣ በአሞሌ አማካይነት ዓለም አቀፍ ክፍያን በመቀበል፣ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በቀላሉ ለዓለም አቀፍ ደንበኞቻቸው ማቅረብ ያስችላቸዋል ተብሏል።

የሞኔታ ቴክኖሎጂስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የምሩ በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው ከዳሸንና ከቪዛ ሳይበር ሶርስ ጋር በመሆን የዳሸን ደንበኞች ከየትኛውም የዓለም ክፍል ዲጂታል ክፍያ ለመቀበልና የንግድ ሥራቸውን በቀላሉ ለመተግበር የሚያስችላቸውን አገልግሎት ማቅረብ መቻላቸው አንድ ዕድገት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂና ትስስር የአገራችን ነጋዴዎች ለዓለም አቀፍ የዲጂታል ንግድ ይበልጥ ቅርብ እንዲሆኑና ዕድሎቻቸውን እንዲያሰፉ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑንም አክለዋል።
የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ፣ ባንኩ ከሞኔታና ሳይበር ሶርስ ጋር በመሆን ይህን አገልግሎት ዕውን ማድረጉን ገልጸው፣ አገልግሎቱ ብሔራዊ ባንክ ወደ አገሪቱ በሕጋዊ መንገድ የሚገባውን የውጭ ምንዛሪ መጠን ለማሳደግ የያዘውን ዕቅድ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

አቶ አስፋው በንግግራቸው ብሄራዊ ባንክ እየሰጠው ላለው አመራር፣እያደረገ ላለው የፖሊሲ እና መመሪያዎች ድጋፍም እንዲሁም ዳሸን ባንከም ለሚተገብረው ለውጥ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here