ተመድ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል 65 ሚሊየን ዶላር እንዲለቀቅ ወሰነ

0
637

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል 65 ሚሊየን ዶላር እንዲለቀቅ ወስኗል።
ድጋፉ በአገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ምግብ፣ መጠለያ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።
ሚያዚያ 28/2013 የተለቀቀው ድጋፍ በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ ከ16 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ይውላል መባሉን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ከተለቀቀው ድጋፍ ውስጥ 40 ሚሊየን ዶላሩ በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል ሲሆን ቀሪው ደግሞ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ይውላል ተብሏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 131 ሚያዚያ 30 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here