ከጥራት ደረጃ በታች መሆናቸው የተረጋገጡ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደረገ

0
989

በ2013 በጄት ዓመት 10 ወራት በገቢ ምርቶች ላይ በተደረገ የጥራት ቁጥጥር ሥራ መሰረት ከደረጃ በታች መሆናቸው የተረጋገጡ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የገቢና ወጪ እቃዎች ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር እያሱ ስምኦን ገለጹ።
እንደ ኢያሱ ገለጻ ከሆነ 6850 ፍሬ የፍሎረሰንት አምፑል፣39.745 ሜትሪክ ቶን የሶላር ቴክኖሎጂ ምርት፣302 ካርቶን የባትሪ ድንጋይ፣571 ከረጢት የታሸገ ሩዝ፣6 ካርቶን የታሸጉ ምግቦች፣331.4 ሜ.ቶን የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣2602.75 ሜ.ቶን ጋልቫናይዝድ ጥቅል ቆርቆሮ፣182.81 ሜ.ቶን የአርማታ ብረት፣246 ፍሬ የውሃ ፓምፕ ፣700 ካርቶን ሚስማር፣19 ካርቶን ሀይል ቆጣቢ አምፑል፣2477 ኩንታል ሩዝ፣72 ከረጢት የአተር ክክ፣3840 ከረጢት የስንዴ ዱቄት፣49 ሜ.ቶን የዱቄት ሳሙና፣5232 ካርቶን የምግብ ዘይት፣2450 ካርቶን የታሸገ ጁስ፣910 እሽግ ባለ 50ኪ.ግ. የስንዴ ዱቄት ፣49.925 ሜ.ቶን የምስር ምርቶች በተደረገ የላብራቶሪ ፍተሻ እና የኢንስፔክሽን ሥራ ከደረጃው በታች መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም አስመጪና ላኪዎች ባስገኙት የውጭ ምንዛሬ ልክ ማበረታቻ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል


ቅጽ 3 ቁጥር 133 ግንቦት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here