ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ ቅርሶች ከጨረታ እንዲነሱ ተደረገ

0
725

ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ የኢትዮጵያ ቅርሶች ለንደን በሚገኝ ታዋቂ የቅርሰ አጫራች ኩባንያ ለጨረታ ቀርበው ከነበሩበት እንዲነሱ መደረጉን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገለጸ።
ቅርሶቹ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የእንግሊዝ ሜጀር ጄኔራል በሆኑት ዊሊያም አርቦትኖት የተዘረፉ ጥንታዊ የብራና የጸሎት መጽሐፍ፣ ከቆዳ የተሠራ የመጽሐፍ መያዣ ከነመስቀሉ እንዲሁም ከቀንድ የተሠሩ በብር የተለበጡ ጥንታዊ ዋንጫዎች እንደሆኑ ኤምባሲው አስታውቋል ።
እነዚህ ከኢትዮጵያ ተዘርፈው ወደ ለንደን የሄዱት ቅርሶች ባስቢ በተባለ ለንደን በሚገኝ ታዋቂ የቅርስ አጫራች ኩባንያ በኩል ከፍተኛ ተጫራቾች በሚገኙበት ለሽያጭ ሊቀርቡ እንደነበር ታውቋል።
ነገር ግን ኤምባሲው አስቀድሞ በደረሰው መረጃ ቅርሶቹ የኢትዮጵያ ንብረት መሆናችውን በመግለጽ እና ለባለቤት መመለስ እንዳለባቸው በማሳመን በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመመለስ ስምምነት ተደርሷል።
ቅርሶቹ ለአገራችን መንፈሳዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ እሴቶች ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ሲሆን፣ ሌሎች በዘረፋ የተወሰዱ ቅርሶችን በዚህ መልክ በድርድር ለማስመለስ አስተዋጽኦ እንዳለው ኤምባሲው አመልክቷል።
በቀጣይነት በእንግሊዝ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶች እንዲመለሱ ከፍተኛ ድርድሮች እየተደረጉ መሆኑንም ገልጿል።
ከኹለት ዓመት በፊት የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር ከለንደን ወደ አገሩ በክብር እንዲመለስ መድረጉ ይታወሳል።


ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here