የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከግል እጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በተለያየ ግዜ ባደረገው ምክክር መሰረት ቦርዱ የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምኖበት ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺሕ ብር ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት በምርጫ ቦርድ በግል ዕጩ ተወዳዳሪነት እውቅና አግኝተው ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ የግል ዕጩዎች ስማቸውንና አድራሻቸውን፣ እንዲሁም የባንክ አካውንታቸውን ለቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሥራ ክፍል እንዲያስገቡ ቦርዱ ጠይቋል።
ምርጫ ቦርድ እውቅና ለሰጣቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ እንደየ ፓርቲዎቹ ዕጩ ብዛት፣ የሴት ዕጩ ተሳትፎና የአካል ጉዳተኛ ዕጩ አካታችነትን መሰረት ያደረገ ነበር።
ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013



