የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ተኛ ዓመት መደበኛ 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል፡፡
በስብሰባውም ለ2014 ዓመት በቀረበው ረቂቅ በጀት እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል ተብሎ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከምክርቤቱ አባላትም የሚነሱ ጥያቄዎችን ጠቅላይ ሚንስትሩ መልስ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ የምክር ቤቱ ስብሰባ መክፈቻ ላይም የአገር መከላከያ ሰራዊት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የምክር ቤቱ አባላት ያላቸውን ክብር እና አድናቆታቸውን በጭብጨባ ገልፀዋል፡፡



