በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን የተፈጠረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታትና ሰላም ለማስፈን እየተካሄደ ያለው እርቅ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የዞኑ የተቀናጀ ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ ተናገሩ።
በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ጫካ ገብተው ሲንቀሳቀሱ ለቆዩ ታጣቂዎች የተሰጠው የተሃድሶ ስልጠና ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት ሌተናል ጄኔራል አስራት፤ ኮማንድ ፖስቱ ሰላምን ለመመለስ የተለያዩ አማራጮችን መጠቀሙን ገልፀዋል።
እስካሁን ከ2 ሺ 100 በላይ ታጣቂዎች በሁለት ዙር የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።
ታጣቂዎቹ ከህብረተሰቡ ጋር እርቅ በማከናወን ይቅር መባባላቸው በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም ተፈጥሮ መልካም ውጤት ሊመዘገብ መቻሉን ማብራራታቸውን ከኢዜአ ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል።



