በ ኮቪድ 19 ወረርሺኝ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተጓዦች እና ጭነት በማጓጓዝ ከአፍሪካ አየር መንገዶች መምራት መቀጠሉ ተገለፀ

0
578

በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተጓዦችና ጭነትን በማጓጓዝ በአህጉሪቱ የመሪነቱን ቦታ የያዘ አየር መንገድ መሆኑን የአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር አስታወቀ፡፡

እንደ የአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር (ኤ.ፍ.አር.ኤ.ኤ) ዘገባ ኢትዮጵያ በ 2020 ከፍተኛ ቁጥር ያላች መንገደኞችንና ጭነትን በማጓጓዝ፤ ከአፍሪካ አየር መንገዶች በመጀመሪያ ደረጃ ላይ መገኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ አየር መንገዱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል 500ሺ ቶን ጭነት እና አምስት ነጥብ 5 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንደገለፁት “በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ባደረሰው በአለም አቀፉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅትም ቢሆን መሪነታችንን በመቀጠላችን ክብር ይሰማናል፡፡ ይህ የእኛን የመቋቋም እና የመነቃቃታችን መገለጫ ነው፡፡

በአፍሪካ ውስጥም ሆነ ከሌላው ዓለም ጋር ያለ ምንም የበረራ እገዳ ወረርሽኙን ለመዋጋት በሕክምናና ክትባቶች አቅርቦቶች በአየር ትራንስፖርት አማካኝነት በማጓጓዝ ሰዎችን ለመታደግ በተጫወተው ሚና ኮርተናል” ሲሉ በአየር መንገዱ የበላይነት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጓዘው ከፍተኛ የመንገደኞች ትራፊክ ዝርዝርንም ቀዳሚ መሆኑ ተገልጿል።

በአጠቃላይ በአየር ማረፊያው ከተጓጓዙት 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን መንገደኞች መካከልም 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን በኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ውስጥ መጓጓዛቸው የገለጸው የአፍሪካ አየር መንገድ ማህበር፤ አየር መንገዱ በአህጉሩ ውስጥ ብዙ ቁጥር ያላቸው የቀጥታ በረራዎች መኖራቸው ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆን አንዳስቻላት ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here