ዶላርን በኬሚካል እያጠቡ በማባዛት ሊያሰራጩ የነበሩ ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
1019

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታው ድሪም ላይን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ዶላርን በኬሚካል እያጠቡ በማባዛት ሊያሰራጩ የነበሩ ሁለት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቦቹ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል በተደረገ ክትትል በትናንትናው እለት እጅ ከፍንጅ መያዛቸው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ስታፍ ዳይሬክቶሬት ህዝብ ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት አባላት ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ መሰረት ባደረጉት ክትትል ዶላርን በኬሚካል እያጠቡ በማባዛት ሊያሰራጩ የነበሩ ኮንጎዊ እና ካሜሩንያን ግለሰቦች ከነ ኬምካሉና ዶላሩ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻሉም ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here