መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናለኢትዮጵያ የአበዳሪዎች ኮሚቴ በፍጥነት እንዲቋቋም አይ ኤም ኤፍ ጥሪ አቀረበ

ለኢትዮጵያ የአበዳሪዎች ኮሚቴ በፍጥነት እንዲቋቋም አይ ኤም ኤፍ ጥሪ አቀረበ

“ኢትዮጵያ እየጠየቀቻቸው ያሉትን ብድሮች በጊዜው መሰረት መመለስ መቻሏን የሚከታተል የአበዳሪዎች ኮሚቴ በፍጥነት እንዲ ቋቋም የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በጥብቅ ያበረታታል” ሲሉ የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቃል አቀባይ ጌሪ ራይስ ተናገሩ፡፡

በየካቲት ወር 2021 ኢትዮጵያ ከ ጂ20 ሀብታም አገራትና የፓሪስ ክለብ አበዳሪዎች “የጋራ ማዕቀፍ” የብድር ተጠቃሚ ለመሆን ጥያቄ አቅርባ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የብድሩም አላማ ለልማት ወጪዎች በቂ በጀት ማግኘትና የእዳ ጫናን ቀንሶ የእዳ ክፍያ ጊዜዎችን ማሸጋሸግ ሲሆን የኮሚቴው መቋቋም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያን ለማገዝ ያለመ መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች