ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ገድሏል በሚል የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈበት ጥላሁን ያሚ በሞት እንዲቀጣ ጠየቀ፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ሐምሌ 8 የከሳሽ እና የተከሳሽ የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ አስተያየት ለመቀበል ቀጠሮ መያዙን የሚታወስ ነው፡፡
በዚሁ መሠረት ዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ አቅርቧል፡፡
የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈበት ጥላሁን ያሚ የቀደመ ሁለት የወንጀል ሪከርድ እንዳለበት በቅጣት ማክበጃው ተጠቅሷል፡፡
ችሎቱ ተከሳሾች የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ያለማቅረባቸውን ተከትሎ ሀሳብ አለን የሚሉ ከሆነ ከቅጣት ቀጠሮ በፊት እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ አስተያየት መርምሮ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለሐምሌ 20 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡



