የትራስፖርት ሚኒስቴር ሴት ሰራተኞች ህብረት ዓመታዊ አፈፃፀሙን መገምገሙን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታወቀ።
በሀገራችን መንግስት የተዛባ የሥርዓተ ፆታ አመለካከትን ለመለወጥ በቁርጠኝነት የህግ ማዕቀፎችን በመቅረጽና ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ በማድረግ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሁሉም መስኩ ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በትራንስፖርት ዘርፍም ለሴቶች ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና የስራ ዕድል ለመፍጠር ቁልፍ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል።
ስለሆነም የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ከሴት ሰራተኞች ህብረት ጋር በጋራ ለሴት ሰራተኞች የማነቃቂያ እና የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ሰጥተዋል።
ስልጠናው ሴቶች በዘርፉ ንቁ ተሳትፎ ለማበርከት እንዲያስችላቸው ብሎም የህይወት ክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና እንዳገኙ በግምገማው ላይ ተገልጿል።
በተጨማሪም ህብረቱ በ 2013 ዓ.ም ያከናወናቸውን ተግባራት የገመገመ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይም ውይይት ተደርጓል።
በመጨረሻም ህብረቱ ለክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ለህብረቱ መመስረት ላደረጉት አስተዋፅኦ እና በተቋሙ ለውጥ ለነባራቸው ድርሻ የምስጋና ሽልማት ማበርከቱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።







