ሕብረት ባንክ በኦንላየን ባንኪንግ፣ በዳታ ሴንተርና በዲዛስተር ሪከቨሪ ፋሲሊቲ የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ማኔጅመነት ሲስተም የISO/IEC 27001:2013 መስፈርትን በሟሟላት የዕውቅና ሰርተፍኬት ማግኘቱን የአይቲ ኢንፍራስትራክቸር ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ኡስማን ሰኢድ ገልጸዋል።
በዓለም አቀፍ PECB MS ድርጅት ባንኩን በተቀመጡ የISO/IEC 27001:2013 መስፈርቶች መሰረት የባንኩን የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ሲስተም በመመርመር ሰርተፍኬት እንደተሰጣቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ባንኩ የISO/IEC ሰርተፍኬት ማግኘቱ በሚሰጣቸው የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎቶች አስተማማኝ ሥርዓት መዘርጋቱን የሚያረጋግጥና ደንበኞች አስተማማኝ የሆነ የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ማሳያ ነው ብለዋል።
በአገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ከሳይበር ጥቃቶቸ አንጻር ባንኩ የISO/IEC ሰርተፍኬት ማግኘቱ በአገልግሎት አሰጣት ላይ ይበልጥ ስኬታማ እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ ባንኩ የISO/IEC ሰርተፍኬትን መረከቡ የፋይናንስና ሌሎች የባንኩ መረጃዎች ደህንነታቸው መጠበቁን የሚያረጋግጥ እንደሆን አስረድተዋል።
ቅጽ 3 ቁጥር 141 ሐምሌ 10 2013


