እንደ አንድ ልብ ሆነን የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ ተግባር መመከት ይገባናል፡- የሀረሪ ክልል

0
755

እንደ አንድ ልብ ሆነን የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ ተግባር መመከት ይገባናል ሲል የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ በወጣው የአቋም መግለጫ አሳሰበ፡፡

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ህዝብ በማቀናጀት በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣውን የውስጥና የውጪ ትንኮሳን ለማክሸፍ ዝግጁነቱን ይገልፃል፡፡

ወትሮም ቢሆን ለስልጣን እንጂ ለሀገርና ህዝብ ግድ የሌለው አሸባሪው የህውሃት ቡድን ከለውጡ ጅማሮ አንስቶ ሀገሪቱን እንደሚያሻግር ተስፋ የጣሉበትን ሀገራዊ ለውጥ ለመቀልበስ አንዴ ከውስጥና ውጪ ሆነው የኢትዮጵያን ውድቀት ከሚመኙ አካላት ጋር በማበርና በማሰለፍ ሀገሪቱን ለመበታተን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

የጁንታው ሙከራዎች ሁሉ አልሳካ ሲለው የሀገራችንን ምልክት የሉአላዊነታችን ደጀን የአፍሪካውን መመኪያ በሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ጭካኔ በተሞላበት መልኩ በማጥቃት ከሀዲነቱን ዳግም አስመሰከረ።

ሆኖም መላው ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ከሀገር መከላከያ እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ጫካ ለመግባት ተገዶ እና በህዝብ መሀል ተሰግስጎ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ሲፍጨረጨር ቆየ።

ሆኖም መንግስት የክልሉ በሁኔታው የተጎዳው የክልሉ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ በበቂ ደረጃ ተደራሽ እንዲሆን እና አርሶ አደሩም እርሻውን ከተኩስ ድምፅ ነፃ ሆኖ እንዲከውን ታሳቢ በማድረግ የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ለሕዝብ ጥሩ የጥሞና ጊዜ የፈጠረ መሆኑን አምኖ ሲደግፍ ቆይቷል፡፡

ሆኖም ግን ሕወኃት/ጁንታ ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ ለተደረገዉ ጥሪ ወደ ጎን በመተው ህዝብ ቦታ እንደሌለዉ ጦርነት በማወጅና ትንኮሳ በመፈፀም በግልፅ በማሳየት ዛሬም እንደ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል።

ጁንታው በተባበሩት መንግስታት የወጣዉን የሕፃናት መብት ድንጋጌ በመጣስ የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ለጦርነት በመማገድ ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አዛውንቶችን፣ እናቶችንና የሐይማኖት አባቶችን በማሰለፍ በእልቂታቸዉ የጀግንነት አክሊል ለመድፋት ይሞክራል፡፡

በመሆኑም በተለይም በአሁኑ ወቅት መላው ኢትዮጵያውን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሸባሪው ቡድን በሚነዙ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ሳንወናበድ፤ ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር፤ እርስበእርስ በመመካከርና በመደጋገፍ፤ የተቃጣብንን አገራዊ ጥቃት በህብረትና በአንድነት፤ እንደ አንድ ልብ ሆነን የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ ተግባር መመከት ይገባናል።

የክልላችን ህዝብና መንግስትም በሀገር ህልውና ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት እንደወትሮው ያልተቆጠበ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደር ያረጋግጣል።

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ህብረት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ሐምሌ 2013

ሀረር

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here