ማይክሮሶፍት ኩባንያ በወርሃዊ የጥቃት ተጋላጭነት ክፍተት መሙያ ፕሮግራሙ መሰረት በሐምሌ ወር 2021 ፕሮግራሙ ለ117 የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶች መጠገኛ አቅርቧል።
ከመጠገኛዎቹ መካከል ዘጠኝ የሚሆኑት ቀድመዉ ያልተለዩ የሶፍትዌር ጉድለቶችን ሲሆኑ ከስድስቱ ውስጥ አራቱ ደግሞ አደገኛ እና ንቁ ጥቃት አድራሽ ናችዉ።
ተጋላጭነቶቹ በሶፍትዌር ክፍተቶች ሳቢያ ተጎጂ የሆኑ የኮምፒዉተር ስርዓቶችን የመቆጣጠር አቅም የሚሰጣቸዉ እንደሆነም ታውቋል።
በያዝነዉ ሃምሌ ወር ከቀረቡ 117 የሶፍትዌር ክፍተት መጠገኛዎች 13ቱ እጅግ ወሳኝ በሚል የቀረቡ ናቸው። 103ቱ የክፍተት መሙያዎች ደግሞ አስፈላጊ የሚል ደረጃ ያላችዉ ሲሆን፤ ቀሪዉ አንዱ ደግሞ መካከለኛ ተብሎ የተሰየመ ነዉ።
የሃምሌ ወር ዝመና ለተለያዩ የማይክሮሶፍት ምርቶች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚዉል ሲሆን ከእነዚህ ምርቶች መካከልም ዊንዶውስ (Windows)፣ ቢንግ (Bing)፣ ዳይናሚክስ (Dynamics)፣ ኤክስቼንጅ ሰርቨር (Exchange Server)፣ ኦፊስ (Office)፣ ለስክሪፕት ኢንጂን (Scripting Engine)፣ ዊንዶውስ ዲ ኤን ኤስ (Windows DNS) እና ቪዥዋል ስቱዲዮ ኮድ (Visual Studio Code) እንደሚገኙበትም ታውቋል።
የሃምሌ ወር የጥቃት ተጋላጭነት ካለፉት ግንቦት እና ሰኔ ወራት አንጻር ከፍተኛ የሚባል ተጋላጭነት የታየበት ሲሆን የሃምሌ ወር 117 ተጋላጭነት ከግንቦት 2021 ከተከሰተዉ 55 ተጋላጭነት እና በሰኔ ወር ከተገኘዉ 50 የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት አንጻር ከፍተኛዉ ነዉ።
እርስዎም ኮምፒዉተርዎን ለማዘመን በመጀመሪያ “start” የሚለዉን አማራጭ በመመምረጥ “setting” የሚለዉን መጫን፤ በመቀጠል ከቀረቡት አማራጮች window update የሚለዉን በመምረጥ የቀረበሎትን window update ይጫኑና “check for update” በመጫን የደህንነት ዝመናዉን በመተግበር ራሰዎን ከሳይበር ከጥቃት ይከላከሉ ሲል የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስታውቋል።



