የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍ እና የልማት ማህበር ሀምሌ 18 ቀን 2013ዓ.ም ለመከላከያ ሰራዊታችን ያለውን ወገናዊነት እና አብሮነት የሚገልፅበት ቀን እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ

0
546

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍ እና የልማት ማህበር ሀምሌ 18 ቀን 2013ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ በሀገሪቱ ባሉት 287ቱም ቅርንጫፎቹ ለመከላከያ ሰራዊታችን ያለውን ወገናዊነት እና አብሮነት የሚገልፅበት ቀን እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ።

ማህበሩ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መግለጫ ሰጥቷል

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሀምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ በመግለጫው እንደተናገሩት ፣ ኢትዮጵያ ሀገራችን ያለችበት ሉአላዊነት እና አንድነቷ ላይ የተጋረጠውን ፈተናዋን እና ህዝባችን እየከፈሉ ያሉትን ዋጋ በውትድርና ሙያችን ስንመዝነው ወቅቱ በነፃ ሲሞትላትና ደሙን ሲያፈስላት ለነበረ ሰራዊት ቀርቶ ንፁህ ህሊና ላለው የሰው ፍጥረት ለሆነ ግልፅ መሆኑ ይታወቃል።

ለዚሁ እኩይ ተግባር ኢትዮጵያዊያን በአንድ የእናት ሀገር ጥሪ ሰምተው የየክልሎች ልዩ ሀይሎች ኢትዮጵያዊነትን የማይደራደሩበት የጋራ ሀብታቸው መሆኑን ለማሳየት የተሰለፉበት ወቅት በመሆኑ እኛ የቀድሞው ሰራዊት እንኮራባችኋል ብለዋል።

በዚህም መሰረት የልማት ማህበሩ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ በመሳተፍ ሀገራዊ ተልእኮውን ለመወጣት ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል።

1/ በማሰልጠኛ ተቋም ብቃት ያለው ወታደራዊ እና ሀገራዊ ራእይ የሰነቀ

ወታደርን የማብቃት ስራን ማሠራት

2/ የአካባቢ እና ከፍተኛ የመንግስት ተቋማትን በጠንካራ የጥበቃ ስርአት

ማስከበር

3/ የመከላከል ውጊያ ላይ መሳተፍ

4/ በአመራር ሰጭነት ማገልገል

5/ ሁሉንም አቀፍ ወታደራዊ ሙያን ለኢትዮጵያውያን ግንዛቤ መፍጠር

6/ የከተማ የፀጥታ ስራ በተገቢው መንገድ እገዛ ማድረግ ላይ

ተሰማርተው ተልዕኮን ለመወጣት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የማህበሩ 287ቱም ቅርንጫፎች ሀምሌ 18 ቀን 2013ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ ለመከላከያ ሰራዊታችን ያለንን ወገናዊነት እና አብሮነታችንን የሚገልፁበት ቀን እንዲሆን መወሰኑን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here