በኢትዮ-አሜሪካውያን የተቋቋመው ‘የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትወርክ’ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደብዳቤ ጻፈ

0
1156

በአሜሪካን ሃገር በሚኖሩ ኢትዮ-አሜሪካውያን የተቋቋመው ‘የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትወርክ’ አስተዳደራቸው በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ በመቃወም ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደብዳቤ መፃፉን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው ከሆነ ኔትወርኩ በደብዳቤው አሜሪካና ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት ያላቸውና የኢትዮጵያ ወታደሮችም ከአሜሪካን አቻዎቻቸው ጎን በኮሪያ ጦርነት ወቅት በመሰለፍ መሰዋታቸውን አንስቶ፣ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል በኢትዮጵያ ላይ እየተላለፉ ያሉ እርምጃዎች ስጋት እንደፈጠሩበት ገልጿል፡፡

ደብዳቤው አክሎም በአሁኑ ወቅት በመንግስት በአሸባሪነት በተፈረጀው፤ በሕወሃት አገዛዝ ወቅት ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ ጫና፣ እንግልት እንዲሁም ለዘር ማጽዳትና መፈናቀል ተጋልጠው እንደነበር ጠቅሶ፣ ቡድኑ እንደለመደው በዓለም አቀፍ ህግ በወንጀል የሚያስጠይቀውን ህጻናትን ለውትድርና የማዋል ተግባር በመፈጸም ላይ እንዳለ አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት ይህንን ተግባር እንዳላየ ማለፉ ተገቢ አለመሆኑን ኔትወርኩ ገልጾ፣ የአሜሪካ መንግስት በሕወሃት አማካኝነት እየተፈጸመ ያለውን ልጆችን ለውትድርና የማዋል ተግባርን እንዲኮንን ጠይቋል፡፡

ተመሳሳይ ተግባራት በዝምታ የሚታለፉ ከሆነ በአስተዳደራቸውም ሆነ በአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ ሚና እና ተቀባይነት ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ እንደሚያልፍም ማሳሰቡን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

የደብዳቤው ሙሉ ቃል ከመረጃው ጋር ተያይዞ ቀርቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here