10ቱ ግዙፍ በውሃ ኃይል ኤሌክትሪክ አመንጪ ግድቦችና መገኛቸው

0
1184

የውኃ ኃይል በዓለማችን ትልቁ ታዳሽ የኃይል ምንጭ ነው። በዓለማቀፉ የኃይል ኤጀንሲ (IEA) መሠረትም ይህ እስከ የአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2024 ድረስ እውነት ሆኖ የሚቆይ ነጥብ ነው።
በዐስርቱ ዝርዝር የሚገኙትና ሥማቸውን ለመጥራት የሚያስቸግሩት በውሃ ኃይል ኤሌክትሪክ አመንጪ ግድቦች፣ የየአገራቱን ከፍተኛ የኃይል ፍጆታ መሸፈን የቻሉ ናቸው። ከእነዚህ መካከል ቻይና የአራቱ ግድቦች (ስሪ ጎርጅ ግድብ፣ ዢሎውዱ፣ ዢንጂባ እና ሎንግታን) ባለቤት ናት። ብራዚል ከፓራጓይ ጋር በድንበር ከምትጋራው ግድብ (ኢታይፑ) ውጪ ኹለት ግድቦችን (ቤሎ ሞንቴ እና ቱኩሩይ) በዋናነት ገንብታ እየተጠቀመች ትገኛለች።
ቬንዙዌላ፣ አሜሪካ እና ሩስያ እያንዳንዳቸው አንድ (ጉሪ፣ ግራንድ ኮውሊ እና ሳያኖ ሹሼንስካያ ) ግዙፍ ግድቦችን በዓለም ዐስርቱ ግዙፍ ግድቦች ዝርዝር አስመዝግበዋል። አሁንም ታድያ በተለያዩ አገራት እየተሠሩ ያሉ ተጨማሪ ግዙፍ ግድቦች ይገኛሉ።


ቅጽ 3 ቁጥር 142 ሐምሌ 17 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here