በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሰመራ መግባት ጀምረዋል፡-አል ዐይን

0
949

በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ አፋር ክልል፤ ሰመራ ከተማ መግባት መጀመራቸው ከሰመራ ከተማ ነዋሪዎች መስማቱን አል ዐይን የተሰኘው የዜና ምንጭ አስነብቧል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ልጆች ያሏቸው ወላጆች፤ መንግስት በዩኒቨርሲቲዎቹ ባሉ በተማሪዎቹ ዙሪያ እልባት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ባሳለፍነው ሳምንትም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ልጆቻቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻችላቸው በሰልፍ መጠየቃቸውም የሚታወስ ነው፡፡

አሁን ላይ በትግራይ ክልል ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል 325 የሚሆኑት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ አቀባበል እንደተደረገላቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሰመራ ከተማ የሥራ ኃላፊ ነግረውኛል ሲል ነው አል ዐይን አማርኛ በዘገባው ያሰፈረው፡፡

ዛሬ ሰመራ የገቡት ተማሪዎች ወደ የቤተሰቦቻቸው እየተሸኙ መሆኑ የስራ ኃለፊው እንደገለፁም በዘገባው አስነብቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here