በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ የገቡ 34 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Views: 386

በአንድ ሚኒባስ ተሸከርካሪ የነዳጅ ማስቀመጫ ታንከር ውስጥ በማስቀመጥ ወደ አዲስ አበባ የገቡ 34 ሽጉጦች ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውለዋል። መነሻውን ሐረር ከተማ ያደረገው ኮድ 3- 66951 ኦ/ሮ የሆነ ሐይ ሩፍ ሚኒባስ ተሸከርካሪ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ውስጥ ለዚሁ ዓላማ ተብሎ በብረት በጥንቃቄ በተሰራ ስፍራ በማኖር ወደ አዲስ አበባ ማስገባት እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመሆን ባደረጉት ክትትል 33 ስታር ሽጉጥና አንድ ማካሮቭ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል። ሽጉጦችን ከላይ በተጠቀሰው የተሸከርካሪው ክፍል በማድረግና በፕላስቲክ በመጠቅለል ወደ አዲስ አበባ የገቡትን ሽጉጦች ኅዳር 16/2012 በተሸከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥ ስር መዋል እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ አያይዞም ሽጉጦቹ በባለሙያ በታገዘ እና አራት ሰዓታትን በፈጀ እልህ አስጨራሽ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ገልጿል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com