በሴቶች 1500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር እና አትሌት ለምለም ኃይሉ ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።
ትናንት ለሊት በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሴቶች 1500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር በሶስት የተለያዩ ምደቦች ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ሲያልፉ ድርቤ ወልተጂ ማጣሪያውን ማለፍ አለመቻሏ ታውቋል።
አትሌት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር በ4:04.12 እና አትሌት ለምለም ኃይሉ በ4:05.49 በተመሳሳይ ከየምድባቸው 5ኛ ደረጃን በመያዝ ቀጣዩን የግማሽ ፍፃሜ ውድድር የተቀላቀሉ ሲሆን፥ ውድድራቸውን ረቡዕ እኩለ ቀን ላይ እንደሚያደርጉ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሌላኛው ምድብ ውድድሯን ያደረገችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ4:10.25 በሆነ ሰዓት 12ኛ ደረጃን በመያዟ ማጣሪያውን አለማለፏም ታውቋል።





