ሁለት ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ምርጥ 10 ወጣት የህዋ ተመራማሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

0
887

ትንሳኤ አለማየሁ እና ቤተልሔም ግርማ የተባሉ በህዋ ምርምር ላየ የተሰማሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በአፍሪካ ምርጥ 10 እድሜያቸው ከ30 በታች የሆኑ የህዋ ምርምር ባለሙያዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን ኢንሳይድ አፍሪካ ዘግቧል።
ትንሳኤ በአሁኑ ሰዓት ከስፔስ ቴክኖሎጂ ፎር ኧርዝ አፕሊኬሽንስ (STEA) ጋር በመቀናጀት ሳተላይት ላይ ተንተርሶ የእርሻ ግብርና እና ጤና ቁጥጥር አገልግሎቶችን በሚሰጥ ስርዓት ላይ እየሰራ ይገኛል።
የ29 ዓመቷ ቤተልሔም ግርማ በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ በረዳት ተመራማሪነት እያገለገለች የምትገኝ ሲሆን በተለያዩ የምህንድስና ፕሮጀክቶች ላይ ተሳታፊ ሆና እየሰራች መሆኑም ታውቋል።
የ23 ዓመቱ ትንሳኤ በበኩሉ የመጨረሻ ዓመት የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪና በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነው።
ተቋሙ ባወጣው ከ30 ዓመት እድሜ በታች የሚገኙ ምርጥ አፍሪካዊ የህዋ ሳይንስ ምርምር ላይ ከሚገኙት ዝርዝሩ ውስጥ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከአልጄሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ሞሪሺየስ፣ ዚምቧብዌ፣ አንጎላ እና ሴራሊዮን የተውጣጡ ወጣት ባለሙያዎች የተካተቱ ሲሆን ግብፅ እና ኢትዮጵያ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ወጣቶችን በማስመረጥ ብቸኛዎቹ ሀገራት ሆነዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here