ድጋሚ ቆጠራ እንዲደረግባቸው የተባሉ ምርጨ ክልሎች ቆጠራ አካሄዱ

0
1192

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድጋሚ ቆጠራ እንዲከናወን ባዘዛባቸው አምስት የምርጫ ክልሎች ቆጠራ መካሄዱን የቦርዱ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ ከወሰነባቸው አስር የምርጫ ክልሎች በአምስት ምርጫ ክልሎች ዳግም ቆጠራ መካሄዱ ተገልጿል።
ምርጫ ቦርድ የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ውጤት ይፋ ባደረገበት ሐምሌ 3/2013፣ ውጤት ሊቀይሩ የሚችሉ የአሠራር ግድፈቶችን መርምሮ ዳግመኛ ቆጠራ እንድደረግ መወሰኑ የሚታወስ ነው። የድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ ከተወሰነባቸው አስር የምርጫ ክልሎች ውስጥ ሦስቱ ለተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ የተከናወነባቸው ናቸው። የፓርላማ ምርጫ የተከናወነባቸው እነዚህ የምርጫ ክልሎች፣ በደቡብ እና አማራ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ናቸው።
በደቡብ ኦሞ ዞን በሚገኘው በባኮ ጋዘር አንድ ምርጫ ክልል፣ ለፓርላማ መቀመጫ ለመወዳደር ዕጩዎችን ያቀረቡት አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች መሆናቸውን የምርጫ ቦርድ መረጃ ያሳያል። ፓርቲዎቹ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣ ሕብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ናቸው። የሕብር ኢትዮጵያ ተወካይ ከመጀመሪያው ቀን በኋላ “በግል ምክንያት” ቆጠራውን አለመታዘባቸው ተገልጿል። የቀሪ ሦስቱ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እና አምስት ምርጫ አስፈጻሚዎች ግን ቆጠራው እስከሚጠናቀቅ መገኘታቸው ተመላኳቷል።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here