ባልደራስ ህወሓትን ከመቃብር ለማንሳት የሚደረገውን የዓለም ዐቀፉ ሴራ መመከት እንደሚገባ ገለጸ

0
793

ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን አሁን ላለችበት ሁኔታ የዳረጋትን ሥርዓት ከመቃብር ለማንሳት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በተባበረ ክንድ መመከት እንደሚገባ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ።
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር በቃሉ አጥናፉ “ትህነግ የአክራሪ ብሔርተኝነት የመጨረሻው ማሳያ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
የመንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ መልካም ቢሆንም አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን አለማቆሙ ለሠላም ቅንጣት ያክል ፍላጎት እንደሌለው ማሳያ እንደሆነም ነው የተናገሩት።
ዓለም ዐቀፉም ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን ለዚህ የዳረጋትን ሥርዓት ከመቃብር ለማስነሳት እያደረገ ያለው ጥረት ፍትሐዊነት የጎደለውና ፍጹም ዓድሏዊ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ቡድኑ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀውን ሕግ ተላልፎ ሕጻናትን ለጦርነት ሲማግድ፣ በአፋር ክልል ሕፃናትን ሲረሽን ያሳየው ዝምታ ምን ያህል ወገንተኛና ዓድሏዊ እንደሆነ ያሳየ በመሆኑ አበክረን እናወግዘዋለን ነው ያሉት።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የውጭ ጠላቶችን ጫና በመቋቋም ሽብርተኛው ህወሓትን ለማጥፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ በማንኛውም መንገድ የመሳተፍ አገራዊ ኃላፊነት እንዳለበትም ተናግረዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 145 ነሐሴ 8 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here