ለአዲስ ዓመት በዓል ምርቶቹን በሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት እንደሚቀርብ ተገለጸ

0
972

ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል በተመጣጣኝ ዋና ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ። ለ2014 ዘመን መለወጫ በዓል የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር ሲሳይ አረጋ ተናግረዋል።
ከተለያዩ ክልሎች የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ከሚያመርቱ ህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች ጋር የገቢያ ትስስር መፈጠሩን የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተሩ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በበዓል ወቅት የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ እስካሁንም የቁም እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ ውጤቶች ፣ቀይ ሽንኩትር፣ በሬ፣ በግ፤ ፍየል ፣ዶሮ፣ እንቁላል ለሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ለመሸጥ በበቂ ሁኔታ ምርት ማቅረባቸውንም ጨምረው ገልፀዋ።
ሸማቹ ማህበረሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ 1 መቶ 48 ህብረት ስራ ማህበራት እና በ10 ዩኒየኖች ምርቶቹን መሸመት እንደሚችሉም ተገልፃል። ለመጪው አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በሁሉም ሊኳንዳ ቤቶች 1 መቶ 56 የእርድ በሬዎች መቅረባቸውንም ምክትል ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 148 ነሐሴ 29 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here