በኢትዮጵያ በስምንት ወራት ውስጥ የ128 ሰዎች የአይን ብርሃን መመለሱ ተነገረ

0
701

በኢትዮጵያ በ8 ወራት ውስጥ በተደረገ የአይን ብሌን ንቀል ተከላ 128 ሰዎች የአይን ብርሀናቸው መመለሱ ተገልፆል፡፡

ሆኖም ግን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአይን ባንክ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደረገ በመሆኑ ልገሳው ከሌሎች ጊዜያት ጋር ሲነፃፀር አናሳ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ባንኩ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 2 ሺህ 651 የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸው ማየት ችለዋል ሲሉ በተቋሙ የአይን ባንክ የግንዛቤ ማስጨበጫ አስተባባሪ የሆኑት ነጋ ደምሴ ተናግረዋል፡፡

በባንኩ 8 ሀኪሞች ብቻ በመኖራቸው እና የለጋሾ ቁጥር አናሳ መሆኑ እያጋጠሙ ያሉ ከፍተኛ ችግር መሆናቻውን ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ፣ሀዋሳ ፣ጅማ ፣ጎንደር እና አርባምንጭ የአይን ብሌን ንቀል ተከላ ህክምና እንደሚደረግ ተገልፆል፡፡

ተቋሙ በ2040 ምንም አይነት የአይን ጠባሳ የተከሰተበት ታማሚ እንዳይኖር ማቀዱን አስተባባሪው ጨምረው ገልፀዋል ሲል ብስራት ሬድዮ ዘግቧል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገ ጥናት ከ300 መቶ ሺህ በላይ የሚገመት መስራት የሚችል ወጣትና ጎልማሳ በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት እንደተጓዳ እና ወረፋ በመጠበቅ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here