አዲስ አበባን በመወከል በዓለም አቀፍ የስእል ውድድር አሸናፊ የሆኑ ታዳጊዎች ሽልማታቸውን ተቀበሉ

0
623

አዲስ አበባን በመወከል በደቡብ ኮሪያዋ ቹንቹን ከተማ በተካሄደው ዓለማቀፍ የስእል ውድድር አሸናፊ የሆኑ ታዳጊዎች ሽልማታቸውን መቀበላቸው ተገለፀ፡፡

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ምክትል ተጠሪ ኪም ሂዮን ዱ በቹንቹን ከተማ ከንቲባ ስም ሽልማቱን ለአሸናፊ ታዳጊዎች አስረክበዋል፡፡

ኪም ሂዮን ዱ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ታሪካዊ ወዳጅነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን አንስተው፤ በአዲስ አበባና ቹንቹን ከተሞች መካከል ያለውን ሁለተናዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here