ከሳዑዲ አረቢያ 449 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

0
659

በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለው ጥረት ቀጥሎ በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ጂዳ 139 ህጻናትን ጨምሮ 449 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል የቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here