በመተከል በ194 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል

0
1186

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ቢኒያም መንገሻ ገለጹ፡፡

ይህ የተገለፀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ እያከናወነ በሚገኘነው 23ኛው ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ሃላፊው በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንዳሉት፤ በመተከል ግጭት ትምህርት ቤቶቹ የተጎዱት በ2013 ሲሆን፤ እነዚህም የመጀመሪያ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ናቸው፡፡

ከዚህ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል የፈራረሱ መሆኑን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ 69 ሺህ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደነበሩ ቢኒያም ጠቅሰዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ከመገንባት ባለፈ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ጭምር ተዘጋጅቶ እየተሠራ መሆኑንም ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው፤ የህወሃት ቡድን በተላላኪዎቹ አማካኝነት በክልሉ ያደረሰውን ጥፋት ከማውገዝ ባለፈ ችግሩ እንዳይደገም ትምህርት ቤቶቹን መልሶ ለመገንባት የተቀናጀ ጥረት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

አመራሮች፣ መምህራን፣ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ወላጆች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተጠናከረ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here