በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ በተደረገው ድርድር አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለጸ

Views: 1106

በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል በአሜሪካ
ዋሽንግተን ዲሲ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ በሚመለከት ሲደረግ በቆየው ድርድር አመርቂ ተጨባጭ  ውጤቶች መመዝገባቸውን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)
በትዊተር ገጻቸው አስታወቁ። በአራት ዙር ሲደረግ የነበረው የሦስቱ አገራት ድርድር ያለ ፍሬ መቋጨቱን ተከትሎ አሜሪካ የከተሙት
የዓባይ ተፋሰስ የላይኛው አገራት በአሜሪካ ድርድራቸውን ሲያካሒዱ የቆዩ ሲሆን ይህንም ተከትሎ ወሳኝ እና ጠቃሚ ውጤቶች የተመዘገቡበት
እንደሆነና ውጤቶችም ወደ ሕጋዊ መስመር እንደሚተረጎሙ ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

በአሜሪካ ሲካሔድ የነበረው ድርድር መጠናቀቁ
የታወቀ ሲሆን እዚህ ውጤት ላይ የተደረሰውም ለበርካታ ጊዜያት የሦስቱን አገራት የውሃ ሚንስትሮች እና ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮችን  እንዲሁም የዓለም ባንክ እና የአሜሪካ ታዛቢዎችንም ያካተቱ ድርድሮች መደረጋቸውን
ተከትሎ እንደሆነም የሚታወስ ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com