ተቋርጦ የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሥም ማዘዋወር በከፊል ተጀመረ

Views: 1393

የአዲስ አባባ ከተማ መሬት እና መሬት ነክ ይዞታ ማረጋገጫ በመዝገብ ተመዝግበው የነበሩ ቤቶችን በዘመናዊ መልክ በመረጃ ቋት ለመመዝገብ ከታኅሳስ 6/2012 ጀምሮ አቋርጦት የነበረውን ሥም ማዘዋወርን ጨምሮ ሌሎችከይዞታ ባለቤትነት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን መጀመሩን አስታወቀ።

 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አመዘጋገብ ስርዓት በወረቀት በመመዝገብ የይዞታ ማረጋገጫ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ እስከ አሁን የተመዘገቡትን የጋራ መኖሪያ ቤት፣ ሪል ስቴቶች እና የቀበሌ ቤቶችን የይዞታ መረጃዎች ወደ ዘመናዊ መረጃ ቋት ለመገልበጥ ከታኅሳስ 6 ጀምሮ በዘመቻ ሲሠራ መቆየቱ ተገልጿል።

ነባሮቹን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ሥራ በሚከናወንበት ወቅትም የመረጃ መጣረስ እንዳይኖር ለማድረግ የጋራ መኖሪያ ቤት ሥም ማዛውር እና ሌሎች ምዝገባዎች ተቋርጠው የቆዩ ሲሆን፣ አሁን በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች አገልግሎቱ እንደተጀመረ ተገልጿል።

ወደ ዘመናዊ የመረጃ ቋት የማስገባቱ ሥራ ከዓለም ባንክ የመጡ የቋሚ ንብረት አመዘጋጋብ ደረጃዎችን እና መስፈረቶችን ለሟሟላት በከተማ አስተዳዳሩ በተሰጠ አቅጣጫ፣ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የመሬት እና መሬት ነክ ይዞታ ማረጋገጫ ማእከላት በዘመቻ መልክ ሲከናወን መቆየቱን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመሬት ይዞታ መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ቢንያም አስራት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ዘዴ የከተማ የይዞታ መረጃ መደራጀቱ ከተማዋን ከሌሎች አቻ ከተሞችጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደሚረዳ የታመነበት ሲሆን፣ በከተማዋ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስየሚፈልጉ የውጪ አገራት አልሚዎችን በመሳብ የከተማዋን ደረጃ ከፍ ለማድረግ እንደሚረዳ የከተማዋን ደረጃ ከፍ ለማድረግ እንደሚረዳ ተገልጿል።

የምዝገባ ሥራውም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሲከናወን ቆይቷል ያሉት ቢንያም፣ የመረጃ መጣረስ እንዲሁም ኹለት ዓይነት መረጃ እንዳይመዘገብ ለማድረግ የይዞታ መረጃ ምዝገባን ጨምሮ ሥም ማዘዋወር እና ሌሎች አገልግሎቶች በታኅሳስ ወር ተቋርጠው እንዲቆዩ ተደርጓል ብለዋል። አገልግሎቱ መቋረጡን ተከትሎ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የተሻሻጡ ግለሰቦች ከሰነዶች ማረጋገጭ ኤጀንሲ ተገቢውን መረጃ ቢያቀርቡም፣ ሥም ለማዘዋወር መቸገራቸውን እንዲሁም ለእንግልት መዳረጋቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል።

አሁን ከአስሩ ክፍለ ከተሞች መካከል በአብዛኛዎቹ አገልግሎቱ እንደተጀመረ የተገለፀ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ግንዛቤ በመፍጠር ታግሶ እንዲቆይ መልዕክት ሲተላለፍ ቆይቷል ብለዋል። እንዲሁም አገልግሎቱ ባልተጀመረባቸው ሌሎች ክፍለ ከተሞች በጥቂት ሲተላለፍ ቆይቷል ብለዋል። እንዲሁም አገልግሎቱ ባልተጀመረባቸው ሌሎች ክፍለ ከተሞች በጥቂት ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ እንዲጀመር ለማድረግ የአዲስ አባባ መሬት እና መሬት ነክ ይዞታ ማረጋገጫ ኤጀንሲ እንደ ማእከል እየሠራ ነው ብለዋል።

ሲተላለፍ ቆይቷል ብለዋል። እንዲሁም አገልግሎቱ ባልተጀመረባቸው ሌሎች ክፍለ ከተሞች በጥቂት ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ እንዲጀመር ለማድረግ የአዲስ አባባ መሬት እና መሬት ነክ ይዞታ ማረጋገጫ ኤጀንሲ እንደ ማእከል እየሠራ ነው ብለዋል።

በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች የመብራት እና የኔትወርክ መቆራረጥ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ እክል ፈጥሯል የተባለ ሲሆን፣ በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ላለመጀመሩ በምክንያትነት እንደሚነሳ ተገልጿል።

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በበኩሉ፣ ክፍለ ከተሞች የጋራ መኖሪያ ቤት ሽያጭ ሥም ማዘዋወር በቁመበትም ጊዜ ጭምር ከክፍለ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ከመንግሥት ወደ ነዋሪው ከተላለፈ አምስት ዓመት መሙላቱ የሚያሳይ መረጃ ይዘው ለቀረቡ ባለጉዳዮች፣ የሽያጭ ውል እና የሰነድ ማረጋገጫ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 63 ጥር 9 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com