የእለት ዜና
መዝገብ

Author: ቢኒያም ዓሊ

“ከሥር አድምጡኝ የሚለው ሕዝብ ካልተሠማ ከላይ ያለው ብቻ ተነጋግሮ ችግር አይፈታም”

እመቤት መንግሥቴ ይባላሉ። ኢትዮጵያ ተወልደውና አድገው ያለፉትን 30 ዓመታት በውጭ አገር የኖሩ ናቸው። አራት መጻሕፍትን ለንባብ ያበቁት እኚህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣ ለበርካታ ዓመታት በሚዲያ ዘርፍ አገልግለዋል። ዕውቀታቸውን ከማካፈል ጀምሮ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፣ የመጨረሻ መጽሐፋቸውን ሽያጪ ለዓባይ ግድብ ገቢ ማስገኛ…

“ከተባበርን ቁስላችን ቶሎ እንደሚሽር እርግጠኛ ነኝ”

የዚህ ሣምንት እንግዳችን በሥፋት የሚታወቁት ባላገሩ ተብለው ነው፡፡ ተሾመ አየለ ሕጋዊ መጠሪያቸውም ነው፡፡ ሰሜን ሸዋ ተወልደው ያደጉት እኚህ ግለሰብ ባላገሩ በሚል ሥያሜ የሚጠራ አስጎብኚ ድርጅት አላቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚከሠቱ ግጭቶችም ሆኑ የተለያዩ አካላቶች በሚሠነዝሩት ጥቃት ፈጥነው ለተጎጂዎች…

“የፋይናንስም ሆኑ የንግድ ሕጎች ከወቅቱ ጦርነት ጋር በሚሔድ መልኩ መሻሻል አለባቸው”

አጥላው ዓለሙ (ዶ/ር) ይባላሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ በወጣትነታቸው ሕንድ አገር በባህር መሐንዲስነት (ማሪን ኢንጅነርነት) ሠልጥነው ለተወሰኑ ዓመታት አገራቸውን በመርከበኛነት ያገለገሉት እኚህ ምሁር፣ በምጣኔ ሐብት ዘርፍ ተምረው ከ1998 ጀምሮ በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሦስቱንም ዲግሪያቸውን…

“ካቀድነው አንዳንዴ 5 በመቶውን ብቻ የምንፈጽምበት ወቅት አለ”

ሠለሞን ዓሊ መሐመድ(ዶ/ር) ይባላሉ። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ ዲፕሎማሲና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው። ማኅበሩ ውስጥ ማገልገል ከጀመሩ 10 ዓመት ያስቆጠሩ ሲሆን፣ ከዛ በፊት በባህል ስፖርትና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ለ16 ዓመት ያህል አገልግለዋል። ዶክትሬታቸውን እንደያዙ የፖለቲካና ፍልስፍና መምህር…

“ልመናን ጠንክሮ በመሥራት እንጂ በዐዋጅ ማጥፋት አይቻልም”

ታደለ ደርሰህ ግርማ ይባላሉ፡፡ የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ(ቪኢኮድ) መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ላለፉት 19 ዓመታት ሠርተዋል፡፡ የዓለም የሠላምና የመልካም ሥነ-ምግባር አምባሳደር የሆኑት እኚህ አንጋፋ የሠብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ፣ በደርግ ዘመን የአየር ኃይል ባልደረባ ከመሆን አንስቶ እስካሁን አገራቸውን በተለያየ መስክ…

“ክትባትን በተመለከተ በማኅበረሰቡ የሚነሱ የተለያዩ ብዥታዎች አሉ”

ቤተማሪያም አለሙ ይባላሉ። በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ጀንደር ፎር ኮሚዩኒኬሽን ፕሮግራም የሚባል ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ምክትል ዳይሬክተር ሆነው ላለፉት ሰባት ዓመታት በማገልገል ላይ ይገኛሉ። የማኅበረሰብ ጤና ባለሙያ የሆኑት ቤተማሪያም፣ በሕክምናው ዘርፍ ከ20 ዓመት በላይ ዩ. ኤስ. አይ. ዲ.ን በመሳሰሉ በተለያዩ…

“ስለራስ ጎበና ያለውን ውዝግብ ፖለቲከኞች ናቸው ያመጡት”

ደቻሳ አበበ (ዶ/ር) ይባላሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የአፍሪካ ጥናትና ምርምር ተቋም የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ታሪካዊ ይዘት ያላቸውን በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን ለንባብ ያበቁት እኚህ መምህር፣ የታሪክ መጽሐፍም አሳትመው ለተደራሲያን አቅርበዋል፡፡ ከዓመት በፊት ለንባብ የበቃው…

ችግራቸው እንደብዛታቸው የጨመረ ተፈናቃዮች

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጦርነት ከተቀሰቀሰና ሕዝብ መፈናቀል ከጀመረ ቢከራርምም እንደሠሞኑ አሳሳቢ የሆነበት ወቅት አልተፈጠረም። በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካቶች ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች በመትመማቸው እነሱን ለመደገፍ የሚደረገውን እርዳታ የማከፋፈልና የማዳረስ ስራውን አዳጋች አድርጎታል። የሚፈናቀለው ቁጥር በጨመረው ልክ ተጨማሪ ድጋፍ ካመገኘቱ በተጨማሪ፣…

አገር አቋራጭ ጉዞና ፍተሻው

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሕገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ የጦር መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች በዝተዋል። ይህን ለመቆጣጠር በየቦታው የፍተሻ ኬላ ተቋቁሞ የፀጥታ ኃይሎች ከሕብረተሰቡ ጋር በመሆን 24 ሰዓት ይፈትሻሉ። እንዲህ አይነት ፍተሻዎች ወደጦር ቀጠናው በተቃረቡ ቁጥር እየጨመሩ ይመጣሉ። ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ…

“ደሞዝ እያገኙም ከተቸገሩት ጋር ተጋፍተው እርዳታ የሚቀበሉ አሉ”

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በኢሳት ዜናዎችን በመዘገብና በማቅረብ እንዲሁም ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ ለተመልካች በማድረስ የሚታወቅ ባለሙያ ነው። ኢሳት ወደአገር ውስጥ ከገባ ጊዜ አንስቶ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አብዛኛው ጋዜጠኛ የማይደፍራቸውን ዘገባዎች ፈልፍሎ በማውጣት ስሙ በብዙዎች ዘንድ በአድናቆት ይነሳል። ኦነግ ወደአገር ገባ ከተባለ ጊዜ…

ከሞት ያመለጡ ተፈናቃዮች

ዓመት ሊሞላው የተወሰኑ ቀናት የቀሩት በሰሜኑ የአገሪቱ አካባቢ የተነሳው ጦርነት እስካሁን የበርካቶችን ሕይወት አሳጥቷል። የሞት ጥላ አንዣቦባቸው የኖሩበትን ቀዬ ጥለው የተሰደዱና ተፈናቃይ ተብለው በየመጠለያ ጣቢያውና በየዘመድ አዝማዱ፣ እንዲሁም በየዱሩ ኬንዳ ወይም ሸራ ወጥረው ለመኖር የተገደዱ በጣም በርካታ ዜጎች አሉ። ጦርነቱ…

የቡራዩና አዲስ አበባ ወጣቶችን ግጭት ለማስቆም የተደረጉ ውይይቶች ውጤታማነት

በኢትዮጵያ ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ በርካታ ጥቃቶችና ግጭቶች በተለያዩ አካባቢዎች ተከስተዋል። ከነዚህ መካከል እንደመጀመሪያ የሚቆጠረውና በብዙዎች ዘንድ ተስፋ ያስቆረጠው ክስተት የተፈጠረው እዚሁ ዋና መዲናዋ አዲስ አበባ ውስጥ ነው። በስደት የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ለመቀበል በነበረ ሒደት፣ “ቀለም አንቀባለን! አትቀቡም!” በሚል…

“ህወሓቶችን ያጎለመሳቸውና ቦታ የሰጣቸው መንግሥት ነው”

ቴዎድሮስ አያሌው ይባላሉ። ከ1994 ወዲህ ባሉት ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው። የ2002ቱን ምርጫ ተከትሎ ለ7 ዓመታት በእስር ላይ ቆይተዋል። ከእስር ከተፈቱ ወዲህ ዲሞክራሲ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን ትግል አድርገዋል። ከተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች የተፈናቀሉ ስደተኞች እርዳታ እንዲያገኙ በማስተባበርም ይታወቃሉ። ከሠሞኑም በመንግሥት…

የደን ሽፋናችን እውነታ

ደን ለዓለማችን አስፈላጊ ነው ብሎ ለማስረዳት መሞከር ሳንባ ለሰው ልጅ አስፈላጊ ነው ብሎ ለማስተማር እንደመሞከር ነው። የተክሎች አስፈላጊነትን ከልጅነታችን እየተማርን ብናድግም የደን መመናመንን ግን እንደሕዝብ ማስቀረት ሳንችል አሁንም ሽፋኑ እያሽቆለቆለ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። የዓለም ምግብ ድርጅት(FAO) በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው ሪፖርት…

“መንግሥት ዕርምጃ መውሰድ የጀመረው በጣም ዘግይቶ ነው”

አርዓያ ተስፋማርያም የሕወሓትን ባለሥልጣናት ሥራ በማጋለጥ የሚታወቁ አንጋፋ ጋዜጠኛ ናቸው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለውጡን ለማገዝ ወደ አገር ቤት ተመልሰው የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ። በተለያዩ ሚዲያዎች እየቀረቡ ሰው ያልሰማቸውን ታሪኮች በማቅረብ ይታወቃሉ። በትግራይ ጊዜያዊ መስተዳድር ስር የትግራይ ቲቪ ኃላፊ ተደርገው በአጭር…

“በብቃት ሠራዊቱን የሚመራ አመራር መዘጋጀት አለበት”

ኃምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ ይባላሉ። በ1973 የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊትን ተቀላቅለው እስከ 1983 ድረስ አገራቸውን በውትድርናው መስክ አገልግለዋል። አብዛኛውን የወጣትነት ዕድሜያቸውን ኤርትራ ውስጥ በውጊያ ያሳለፉት እኚህ የቀድሞ ሠራዊት አባል፣ ከመንግሥት ለውጡ በኋላ በርካታ የመከራ ወቅቶችን አሳልፈዋል። ከቀን ሥራ ጀምሮ የተለያዩ…

“ምዕራባውያኑ አፍሪካን የመቀራመት አዝማሚያ እያሳዩ ነው”

ስለአባት ማናዬ ይባላሉ። ስለምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ሁናቴ በርካታ ጥናቶችን በማካሄድ የተለያዩ መጻሕፍትንና ጥናታዊ ጽሁፎችን አቅርበዋል። ላለፉት ስምንት ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን፣ አባይን እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድና የመካከለኛው ምስራቅ የዐረብ አገራት መንግስታትን በተመለከተ ጠለቅ ያለ ዕውቀት አላቸው። ከአዲስ ማለዳው ቢንያም…

የአገር ውስጥ ቱሪዝምና መሰናክሎቹ

ቱሪዝም ለአንድ አገር ዕድገት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል። ከጎብኚዎች በሚገኝ ገቢ አገራቸውን የሚያስተዳድሩ በርካታ አገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ አነስተኛ ገቢንም እያገኙ ዘርፉን ትኩረት ሳይሰጡት በርካታ መስህቦቻቸውን የሚያባክኑ አገራት በርካታ ናቸው። ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪኳንና ታይተው የማይጠገቡ የተፈጥሮ ስጦታዎቿን ለጎብኚዎች አመቻችታና…

“ከኤርትራ ጋር ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው ያስታረቀን”

ሻምበል ኤልያስ ሥፋቱ ይባላሉ። ሲዳማ ተወልደው ዕድሜያቸው ሲደርስ የውትድርናውን ዓለም ተቀላቅለው፣ በቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ውስጥ ሠራዊቱ እስኪበተን ድረስ አገልግለዋል። አብዛኛውን የውትድርና አገልግሎታቸውን ወሳኝ በሚባሉ ጊዜያት ትግራይ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በመሰማራት ፈጽመዋል። የቀድሞው ጦር ሠራዊት ከትግራይ የወጣበት መንገድና አሁን መከላከያ…

የፌደሬሽን ምክር ቤት በጀት እስካሁን በሕገመንግሥቱ መሠረት ጸድቆ አያውቅም ተባለ

የማሻሻያ ረቂቁ የመገንጠል መብትን የሚያስተናግድበት አንቀፅ አካቷል በሕገመንግስቱ አንቀፅ 65 መሰረት የፌደሬሽን ምክር ቤት በጀት በተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ቢታዘዝም እስካሁን በሕጉ መሰረት አለመፅደቁ ተገለጸ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እንደተነገረው የምክር ቤቱ…

“በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ምርጫ መደረግ አልነበረበትም”

ጌትነት ወርቁ ይባላሉ። የእናት ፓርቲ ዋና ጽኃፊ ናቸው። በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ሆነው ፓርቲያቸውን ወክለው በወሎ አምባሰል ወረዳ ይወዳደራሉ። ስለ ምርጫው አጠቃላይ ሂደት፣ ስላጋጠሙ ችግሮችና ስለ ፓርቲያቸው እንቅስቃሴ ከአዲስ ማለዳው ቢኒያም ዓሊ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ስለ ፓርቲያችሁ…

በትግራይ በ76 ሰዎች ላይ ክስ ተመስርቷል 53ቱ ወታደሮች ናቸው ተብሏል

የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ሐሙስ ከሰዓት ጋዜጠኞችን ጠርቶ በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በትግራይ ክልል በመንግስት ወታደሮችና በነዋሪዎች ስለተፈጸሙ ወንጀሎች ማብራሪያ ሰጥቷል። በመንግስት አካላት ክልሉ ውስጥ ተፈጽመዋል ተብለው ስሞታ ሲቀርብባቸው የነበሩ የንጽሃን ግድያዎችና የሴቶች መደፈር እውነትነት እንዳለው መረጋገጡን የፌደራል ዋና ጠቅላይ አቃቤ…

ትንኮሳ የተቀላቀለበት ቅስቀሳ

6ተኛው አገራዊ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ከወጣለት ወቅት አንስቶ እስካሁን ድረስ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል። ምርጫውን ከሚያካሂደው ምርጫ ቦርድ ላይ ከሚሰነዘረው ይልቅ ፓርቲዎች እርስ በርሳቸው የሚካሰሱት ትልቁን ቦታ ይይዛል። ምርጫው ጋር በተገናኘ ከሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አብዛኞቹ በመንግስት ወይ በገዢው ፓርቲ አባላት…

“ግንቦት 20ን በዓል ነው ብሎ ማክበሩ ወንጀል ነው” የግንቦት 20 እና የመስከረም 2 ተቃርኖ

ኢትዮጵያ ብዙ ሺሕ ዓመታት ተከብራ የኖረችበት የዘውድ ስርዓት በተማሪ አመጽ ተጀምሮ በወታደር አድማ ከተወገደ 46 ዓመታት ተቆጥረዋል። የሺሕ ዘመናቱ ስርዓት የተወገደውና በኋላ ደርግ የተባለው ወታደራዊ ቡድን ስልጣኑን የተቆናጠጠው መስከረም 2፣ 1967 ነው። ይህ ቀን የሕዝብ በዓላትና የእረፍት ቀንን ለመወሰን ተብሎ…

‹‹ የምርጫ ሂደቱ በብዙ እንከኖች የተከበበ ዝቅተኛ መስፈርትን የማያሟላ ነው ››

ገለታው ዘለቀ በየነ ይባላሉ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የቢሮ ኃላፊ ናቸው። ፓርቲያቸውን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የምርጫ ከልል 20 ላይ ነው። ስለ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት እንዲሁም ስለፓርቲያቸው ሁኔታ ከአዲስ ማለዳው…

error: Content is protected !!