በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋ ዳግም ተከሰተ

Views: 347

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን በሚገኙ  የተለያዩ አካባቢዎች ላይ  የአንበጣ መንጋ ዳግም መከሰቱን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ገለፀ።

የአንበጣ መንጋው ከዓርብ ጥር 29/2012 ምሽት ጀምሮ ከአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ወደ ክልሉ ደቡባዊ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች መግባቱን በቢሮው  የፀረ ተባዮች ዳይሬክተር አቶ መብራህቶም ገብረኪዳን መናገራቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

መብራህቶም የአንበጣ መንጋው በመስኖ በለሙ ሰብሎችና በእንስሳት መኖ እንዲሁም ዛፎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል በመግለፅ  የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የሚያመላክት መረጃ ለሁሉም የማዳረስ ስራ እንደተሰራ ነው ብለዋል።

መንጋው ጉዳት ከማድረሱ በፊት ለመከላከል እና ከአካባቢው ለማጥፋት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ  መሆኑን ያስረዱ ሲሆን  መንጋውን በአጭር ጊዜ ለማጥፋት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከዚህ ቀደም ያሳየውን የተቀናጀ ተሳትፎ በመድገም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com