የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጃዋር መሃመድን ዜግነት በተመለከተ የህግ ማብራሪያ ጠየቀ

Views: 241

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል የሆኑት ጃዋር መሃመድ የአሜሪካ ዜግነታቸውን ትተው ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በህግ እንዳቀርብ የምገደደው ሰነድ የለም ማለቱን ተከትሎ ቦርዱ የዜግነት አዋጁ አንቀፅ 22 እንዲብራራለት ጠየቀ፡፡

ምርጫ ቦርድ የካቲት 2/ 2012 በፃፈው ደብዳቤ የኢሚግሬሽን እና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ‹‹ባለስጣኑ የሚሰጠው ማብራሪያ ቢገኝ አሁን እጅ ላይ ላለው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ለሚሰጡ ተመሳሳይ ጥያቄዎች አፈታትም እንደሚጠቅም ተመልክቷል›› ሲል ያስነብባል፡፡ ኤጀንሲውም እስከ የካቲት 9/2012 ማብራሪያውን ለቦርዱ እንዲልክ ተጠይቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com