የእለት ዜና
መዝገብ

Author: ኢዮብ ትኩየ

የሽንኩርት ዋጋ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው

በአንድ ሳምንት በኪሎ ከ10 ብር በላይ ጨምሯል በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የቀይ ሽንኩርት ዋጋ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ሸማቾች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። የአስፔዛ ዋጋ በየወቅቱ ጭማሬ እየተስተዋለበት ነው የሚሉት አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ሸማቾች፣ በተለይም ቀይ ሽንኩርትና ቲማቲም ከፋሲካ…

እገታና እንግልት እስከ መቼ?

ሥሙ እንዲጠቀስ አልፈቀደም፤ ታሪኩን ግን አጫወተን። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ የተባለው ቡድን፣ በተለያየ ጊዜ የሚያደርገውን እገታ በተመለከተ በቤተሰቡ ላይ የደረሰውን ነገረን። ታሪኩ እንዲህ ነው፤ የባለታሪካችን ወላጅ አባት በአካባቢው አሉ ከሚባሉ ምሁራን መካከል ተጠቃሽ ነበሩ። ታዲያ ፍርድ…

ኢትዮጵያ በ10 ወራት ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት 153 ሚሊዮን ዶላር አገኘች

ኢትዮጵያ በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት 10 ወራት 153 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘቷን የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ምርምር ልማት ማዕከል አስታወቀ። ገቢው የተሰበሰበው በበጀት ዓመቱ ይገኛል ተብሎ ታቅዶ ከነበረው 178 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፤ በዚህም የእቅዱን 85 በመቶ አሳክቷል ተብሏል። 2014…

በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ቤንዚን ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል ተባለ

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ቤንዚን በቀላሉ ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል ሲሉ ተጠቃሚዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። በዚህም አሽከርካሪዎች በተለይም ደግሞ ቤንዚን በስፋት የሚጠቀሙ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ቤንዚን በቀላሉ በማደያ ማግኘት አለመቻላቸውን ገልጸው፣ አሁን ላይ ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱንና በዚህም ምክንያት መቸገራቸውን ገልጸዋል። ለአብነትም…

የወደሙ የትምህርት ተቋማት ጥገና ስላልተደረገላቸው ትምህርት መጀመር እንዳልተቻለ ተገለጸ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኘው በዋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሕወሓት ሙሉ ለሙሉ እንደወደመና ጥገና ስላልተደረገለት ትምህርት መጀመር እንዳልተቻለ አዲስ ማለዳ ሰምታለች። ተቋሙ በሕወሓት ከፍተኛ ደረጃ ጥቃት እንደደረሰበትና ጥገና ስላልተደረገለት ትምህርት መጀመር እንዳልተቻለ የበዋ አንደኛ ደረጃ…

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ ከ150 በላይ ዜጎች መታሰራቸው ተሰማ

ባሳለፍነው ሚያዚያ 21/2014 ስድስት ሴቶች ተደፍረዋል በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው ወደ አማራ ክልል እንዲወጡ የተገደዱ ከ150 በላይ ንጹሃን ዜጎች በባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ታማኝ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። ሥማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የባምባሲ ወረዳ ነዋሪ ለበርካታ…

በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ግልጽና ኅቡዕ ጥቃቶች እንዲቆሙ ሲል ማኅበሩ አሳሰበ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማኅበር በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ግልጽና ኅቡዕ ጥቃቶች እንዲቆሙ ሲል አሳሰበ። ማኅበሩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ መንግሥት ጋዜጠኞች ሥራቸውን በማከናወናቸው ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግበትን ምስጢራዊ አሠራሩን ሊፈትሽ ይገባል ብሏል። እንዲህ ያለው ድርጊት ለመንግሥትም ሆነ በጠቅላላው ለአገር የሚፈይደው ነገር እንደማይኖር…

ዝውውር ያደረጉ መምህራን የሥራ ልምዳቸው ባለመያዙ ቅሬታ አቀረቡ

ለዓመታት ካገለገሉበት ትምህርት ቤት ወደ ሌላ የትምህርት ተቋማት ዝውውር ያደረጉ መምህራን ከስድስት ወር አገልግሎት በኋላ የሥራ ልምድ ይያዝላችኋል የሚል ቃል ቢገባላቸውም የቀጠሮው ቀን ሲደርስ ልምዱ አልተያዘልንም ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ቅሬታ አቀረቡ። ቅሬታ ካቀረቡት መምህራን መካከል አስናቀ ቤኩማ፣ በአንድ የክፍለ አገር…

በዘጠኝ ወር ውስጥ ወደ ውጭ ከተላከ እንጀራ 36 ሚሊዮን ዶላር ተሰበሰበ

በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ አገር ከተላከ እንጀራ 36 ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘ የምግብ፤ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በዘጠኝ ወራት ውስጥ እንጀራ ከመላክ የተገኘው ገቢ ታቅዶ ከነበረው 29 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያሳየ መሆኑ ተነግሯል። በአሁኑ ወቅት…

በሊሙ ወረዳ የእርሻ መሬት በወቅቱ አለመታረሱ የከፋ ችግር እንደሚያመጣ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በሚሰነዝረው ጥቃት ነዋሪዎቹ መፈናቀላቸውን ተከትሎ፤ በወረዳው ያለው ማሳ የመታረሻ ወቅቱ ማለፉ አሁን ካሉበት ሁኔታ ይበልጥ የከፋ ችግር ሊያመጣባቸው እንደሚችል ነዋሪዎቹ ስጋታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። ስሜ ባይጠቀስ ያሉ የአዲስ ማለዳ የመረጃ ምንጭ፤…

በሕወሓት ታጣቂዎች ቤት የተቃጠለባቸው ከ80 በላይ ዜጎች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለጹ

ቤቶቻቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት በተፈረጀው የሕወሓት ታጣቂዎች የተቃጠሉባቸው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ቦታው ጎረንጎሮ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ የሚገኙ ዜጎች ድጋፍ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። ከ80 በላይ የሚሆኑት እነዚህ ቤታቸው የተቃጠለባቸው…

የ2014 ረመዳን ወር ጾምና ድባቡ

የ2014 ረመዳን ወር ጾምና ድባቡኢትዮጵያ ልዩነታቸው አንድነታቸውን የማይነጥለው አንድነታቸው ልዩነታቸውን የማይጠቀልለው በርካታ የዕምነት ተከታይ ዜጎችን እቅፍ ድግፍ አድርጋ የያዘች አገር መሆኗ የአደባባይ ሀቅ ነው። ታዲያ ይህ ወቅትም የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የረመዳንን ጾም የቁርዓን ሥርዓት በሚፈቅደው መልኩ እየጾሙ ይገኛሉ። ከቀናት በኋላም…

የትምህርት ጥራት ከታች ወደ ላይ ወይስ ከላይ ወደ ታች?

ከሚመጣው 2015 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ባሳለፍነው መጋቢት 26/2014 አሳውቋል። በተያያዘም ‹‹በቀጣይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ተገቢውን ዕውቀት፤ ክህሎትና ስብዕና ያሟላ ምሩቅ ለማፍራት እንደሚያስችልና መውጫ ፈተናው በምሩቃን ፕሮፋይል መሠረት ብቁና ተወዳዳሪ…

በቆቦ ከተማ አንድ ሊትር ቤንዚን 100 ብር እየተሸጠ ነው

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ በቆቦ ከተማ ቤንዚን እስከ አሁን ሲሸጥበት ከነበረው መደበኛ ዋጋ ከእጥፍ በላይ ጨምሮ 100 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተገለጸ። አንድ ሊትር ቤንዚን ከኹለት ወር በፊት 40 ብር ይገዙ እንደነበረና አሁን ግን 100 ብር እንደሆነ…

ጥሬ ጨው ወደ ትግራይ ክልል በሕገ ወጥ መንገድ እየተላለፈ ነው ተባለ

ጥሬ ጨው በአማራ ክልል በሚገኙ የወሰን ስፍራዎች በኩል ወደ ትግራይ ክልል በሕገ ወጥ መንገድ እየተላለፈ መሆኑን ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉ በራያ ቆቦ የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በትግራይና በአማራ ክልል አዋሳኝ ስፍራዎች የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ጥሬ ጨውን ተደብቀው በማስተላለፍ…

በግል ተቋም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሊጀመር ነው ተባለ

በኢትዮጵያ በግል ተቋማት ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የኩላሊት ንቅለ ተከላ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን ‹‹ሊያና ሄልዝ ኬር›› ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ኃላፊዎች ለአዲስ ማለዳ አሳወቁ። ተቋሙ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎቱን በቀጣይ መስከረም ወር 2015 በይፋ የሚጀመር መሆኑን የሊያና ሄልዝ ኬር ዋና…

ከ390 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሠራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ቅሬታ አነሱ

ከ390 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሠራተኞች ድርጅቱ ያደረገው የደመወዝ ጭማሪ ‹ፍትኃዊ ባለመሆኑ› ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። ቅሬታ አቅራቢ ሠራተኞቹ ለአዲስ ማለዳ ያሳወቁት፤ ድርጅቱ የብሩን መጠን ሳይገልጽ ለተከታታይ ወራት ደመወዝ ይጨመርላችኋል ሲል ቢቆይም፤ የደመወዝ ጭማሪው ሲደረግ ግን ለአመራሮቹ እንጂ…

የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ደን በከፍተኛ ሁኔታ እየተመነጠረ መሆኑ ተገለጸ

ከ56 ጥበቃዎች መካከል ያሉት ስምንት ብቻ ናቸው በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የሚገኘው ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ከአምናው በከፋ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ አርሶ አደሮች ተከፋፍለው እየመነጠሩት መሆኑን የፓርኩ ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። አርሶ አደሮች ፖርኩን ከአምናው በከፋ ሁኔታ በዘንድሮው ዓመት መሬቱን…

የጉምዝ ታጣቂዎችና ኦነግ ሸኔ በዘረፉት ንብረት ክፍፍል መጣላታቸው ተገለጸ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤና ቡለን ወረዳ ባሉ ሥፍራዎች የሚንቀሳቀሱ የኦነግና የጉምዝ ታጣቂዎች የዘረፉትን ንብረት ለመከፋፈል ሥምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ከቀደመ ወዳጅነታቸው ወደለየለት ጥላቻ መሸጋገራቸውን በቦታው የሚገኙ ታማኝ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። አንድ ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአዲስ ማለዳ ምንጭ እንደተናገሩት፣…

ከትግራይ ክልል ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የተዛወሩ ተማሪዎች የምረቃ ወረቀት አይሠራላችሁም ተብለናል አሉ

በትምህርት ሚኒስቴር በጦርነቱ ምክንያት ከትግራይ ክልል አራቱም ዩኒቨርስቲዎች ሠላም ወዳለባቸው የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተዛውረው የተቋረጠ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የተደረጉ ተመራቂ ተማሪዎች፣ መመረቃቸውን የሚያሳይ ጊዜያዊ የምረቃ ወረቀት አይሠራላችሁም መባላቸውን ተከትሎ ቅሬታ እንደተሠማቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካካል ዳንኤል በቀለ የተባሉት ተመራቂ፣ የተቋረጠ…

ተወርቶ የሚረሳው የነዳጅ ችግር

በኢትዮጵያ የነዳጅ ዕጥረት በየወቅቱ የሚከሠትና ዘላቂ መፍትሔ ያልተገኘለት ችግር እየሆነ መምጣቱ የአደባባይ ወሬ ሆኗል። ነዳጅን በተመለከተ በተለይም ከጉዳዩ ጋር ቅርብ ትስስርና ኃላፊነት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ ውይይት ሲያደርጉ ማየት ተለምዷል። የችግሩ ቀማሾች በተለያዩ ጊዜያት ቅሬታቸውን ያስተላልፋሉ፤ የዘርፉ ምሁራን ሠፋ ያለ ትንታኔን…

በምሥረታ ላይ የሚገኘው የጃኖ ባንክ አመራሮች ቢሮ ዘግተው መጥፋታቸውን ባለድርሻዎች ገለጹ

አመራሮቹ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔ ስላልሰጠን ነው ብለዋል በምሥረታ ላይ የሚገኘው የጃኖ ባንክ አመራሮች ቢሮ ዘግተው መጥፋታቸውን ባለድርሻዎች ገለጹ በምሥረታ ላይ የሚገኘው የጃኖ ባንክ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የባንኩ ባለድርሻዎች የገዙትን አክሲዮን ገንዘብ ሳይመልሱ ተከራይተውት የነበረውን ቢሮ ለቀው እንደጠፉና ስልካቸውንም እንዳጠፉባቸው አክሲዎን የገዙ…

ቀይ መስቀል ተጠልለው የነበሩ የሕወሓት ታጣቂዎች ለዳግም ጦርነት እንዲሰለፉ እየተገደዱ ነው

ወደ ሱዳንና ካርቱም ሸሽተው የነበሩና ትጥቃቸውን ለሱዳን መከላከያ ሠራዊት አስረክበው ወደ ቀይ መስቀል የተጠጉ የቀድሞ የሕወሓት አባሎች፣ በሕወሓት ታጣቂዎች ተገደው ወደ ጦርነት እንዲሰለፉ እየተደረጉ መሆኑን በሁመራ ወረዳ የሚገኙ ታማኝ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። አለው፣ ዲማ እና ልበዲ በተባሉት አካባቢዎች ከመጋቢት…

ውጤትን መሠረት ያደረገ የድጎማ መርሀ ግብር አደጋ ላይ ይጥላል ተባለ

ምዕራባውያን ለጋሾች ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች የትምህርት ዘርፍ ድጋፍ የሚሰጡበት ውጤት ተኮር የድጎማ መርሃ ግብር (Programme for Results) ውጤታማነቱ እንደታሰበው እንደማይሆን ተነገረ። በመጋቢት 21/2014 በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የወጣው አዲስ ጥናት በውጤት ላይ የተመሠረተ ‹‹የፋይናንሲንግ ፓኬጅ›› የሚጠበቀውን ያህል ውጤታማ እንደማያደርግ የኢትዮጵያን…

ኧረ የዘይት ያለህ!

የኑሮ ውድነት ሲነሳ አሁን ላይ በማኅበረሰቡ አንደበት ቀድሞ ሲነገር የሚሰማው ‹‹ኧረ ዘይት!›› የሚል ማማረር የበዛበት ድምጽ ነው። የዘይት ጉዳይ ምንም እንኳ የኑሮ ውድነት በተነሳ ቁጥር ከቤት ኪራይ፤ ከትራንስፖርት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተዛምዶ ሕዝቡን እያማረረ ያለ ችግር ከሆነ ቢቆይም፣…

10 ሺዎቹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ምን አሉ?

በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የወጡ 10 ሺሕ ተማሪዎች፣ በበጎ አድራጎት በየክልሉ በመዘዋወር በተለያዩ ዘርፎች ማኅበረሰቡን ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል። በጎ ፈቃደኞቹ በየክልሉ በመዘዋወር የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ማኅበረሰባቸውን ማገልገላቸውን የሰላም ሚኒስቴርም በየወቅቱ በሚሰጠው መግለጫ አመላክቷል። በጎ ፈቃደኞቹ ከዩኒቨርሲቲ…

ከሳዑዲ አረቢያ ለሚመጡ ስደተኞች የ561 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ስደተኞች 11 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም ዐቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ካወጣው መረጃ ማወቅ ተችሏል። በኢትዮጵያና በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት፣ ከ100 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው እንደሚመጡ ይጠበቃል። ለተመላሾቹ የዕርዳታ…

የብረታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠን ከ20 ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ብርታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠን ከ20 ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማለቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ። የምርት መጠኑ ከ20 ወደ 10 በመቶና ከዛ በታች ዝቅ ማለቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፊጤ በቀለ…

ከ100 በላይ ቤቶች በ12 ቀናት ውስጥ መቃጠላቸው ተገለጸ

የአባሙሳ ከተማ ነዋሪዎች ሙሉ ለሙሉ ተሰደዋል ከመጋቢት አንድ እስከ 12/2014 ባሉት ቀናት ውስጥ በምሥራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ ሥር የሚገኙ ከ100 በላይ ቤቶች በታጣቂዎች መቃጠላቸውን አስተማማኝ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ሥሜ እንይጠቀስ ያሉ የአዲስ ማለዳ ምንጭ፣ ከመጋቢት አንድ እስከ 12/2014 ባሉት…

ከቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ 300 ዝሆኖች ወደ ኤርትራ መሰደዳቸው ተገለጸ

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ከ300 በላይ ዝሆኖች ወደ ኤርትራ መሰደዳቸውን ፓርኩ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። በፓርኩ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው እንስሳት እንደተሰደዱና በተለይም ዝሆኖች ለገበያ ጥቅም ሲባል ለሕገ-ወጥ አደን እየተጋለጡ ስለመሆናቸው የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ…

error: Content is protected !!