የትምህርት ቤት ጫማና ቦርሳ ዩኒፎርም ፕሮጀክት በአገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

0
558

ሰኞ ታህሳስ 18/ 2014 (አዲስ ማለዳ) የትምህርት ቤት ጫማና ቦርሳ ዩኒፎርም ፕሮጀክት በአገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በጋራ ባዘጋጁትና በአገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ በታቀደው የት/ት ቤት ጫማና ቦርሳ ዩኒፎርም ፕሮጀክት ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከከተማ አስተዳደርና ከክልል ኢንተርፕራዞችና ኢንዱስትሪ ቢሮዎች እንዲሁም በዘርፉ ከተሰማሩ አምራቾች ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበል እንደገለጹት አገራችን ብዙ ቢሊዮን ዶላር አውጥታ ከውጭ የምታስገባውን የቆዳ ምርት በአገር ውስጥ ምርት ለመተካትና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ከመቀነስ፣ የአምራች ኢንዱስትሪን የማምረት አቅም ከማሳደግ እንዲሁም የሥራ ዕድል ከመፍጠር አንጻር የፕሮጀክቱ ፋይዳ ትልቅ ነው፡፡

በአገር ውስጥ ምርት ጫማና ቦርሳ ዩኒፎርም በመጠቀም ተማሪዎች አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማህበራዊ ጤንነታቸው ተጠብቆ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ያሉት ሚኒስትሩ በት/ት ቤቶች ተማሪዎችና ህብረተሰቡ ዘንድ የአገር ውስጥ ምርት ተፈላጊነትን ከመጨመር አንጻር ብዙ የግንዛቤ ስራዎች መስራት እንደሚጠበቅም አሳስበዋል፡፡

“በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባንዳዎች የተቃጡብንን የኢኮኖሚ ጫናዎች መቋቋም የምንችለው የአገር ውስጥ ምርቶችን መጠቀም ስንችል ነው ያሉት መላኩ በጦርነቱ ወቅት ያገኘነውን አንድነት በኢኮኖሚ ግንባታውም መድገም አለብን” ማለታቸውንም ከኢፌደሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፕሮጃክቱ በፖሊሲና ስትራቴጂ መመራት እንዳለበትና በአዲስ አበባ መስተዳዳር ሲተገበር የቆየውን ተሞክሮ ክልሎችም ወደ ራሳቸው በመውሰድ መተግበር እንዳለባቸው መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት ላይ የመግባቢያ ሥምምነት መፈራረማቸውም ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here