ማራቶን ሞተር ለመከላከያ ሰራዊት የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

0
730

ማክሠኞ ታህሳስ 19/ 2014 (አዲስ ማለዳ) ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ማራቶን ሞተርስ ድጋፉን ያደረገዉ በዛሬዉ ዕለት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማዕከል ባስመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ ሲሆን፤ በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በኩል ለመከላከያ ሰራዊት አስረክቧል።

በመርሃ ግብሩም ማራቶን ሞተርስ ለሚያመርታቸዉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉን የቻርጅ ማዕከል አስመርቋል።

ማራቶን ሞተርስ ዛሬ ካስመረቀዉ የቻርጅ ማዕከል በተጨማሪ አዳዲስ ሞዴሌ ተሽከርካሪዎችን አስተዋዉቋል።

በዓመት 10 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የማምረት አቅም ያለዉ ማራቶን ሞተር፤ አሁን ላይ ኹለት ሺሕ ተሽከርካሪዎችን በዓመት እያመረተ መሆኑም ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here