ምንጭ፤ ትራቭል ሌዠር 2021
አዲስ ዓመት መቃረቡን ተከትሎ የተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን እንዲሁም የዜና አውታሮች የቀደመው ዓመት ምን ተፈጠረ የሚለውን በማንሳት የዓመቱን የምርጦች ዝርዝር ይፋ ማድረጋቸው የተለመደ ነው። በዚህ መሠረት ትራቭል ሌዠር ባወጣው መረጃ፣ የጎብኚዎችን አስተያየት መነሻ አድርጌና ለሦስት ዓመታት ሰብስቤ በተረዳሁት መሠረት መቶ ምርጥ የተባሉ በዓለማችን የሚገኙ ሆቴሎች እነዚህ ናቸው ሲል ይፋ አድርጓል። ከነዛ መካከል ዐስርቱ ከላይ የተቀመጡት ናቸው።
በዚህ ዝርዝር ከካረቢያን እስከ ደቡብ ምሥራቅ እስያ እንዲሁም ከአፍሪካ እስከ ደቡብ አሜሪካ ያሉ ሆቴሎች ተዳስሰዋል። ሆቴሎቹ በሚሰጡት አገልግሎት ጥራት፣ ባላቸው የአገልግሎት ዓይነት እና በእንግዳ አቀባላቸው ነው ጎብኚዎችም የዳኟቸው።
በዚህ ዝርዝር ሕንድ 12 ሆቴሎች በዝርዝሩ የተካተቱላት በመሆን ቀዳሚ ናት። ከሕንድ በቀመጠል በካረቢያን የሚገኙ 7 ሆቴሎች በዝርዝሩ ውስጥ ተገኝተዋል። አፍሪካ ኬንያ በሚገኘው ‹ማሃሊ ምዙሪ› ሆቴል የተነሳ በዚህ የመቶ ዝርዝር ውስጥ ልትካተት ችላለች። በደረጃም ሆቴሉ በቀዳሚነት ይገኛል።
ቅጽ 4 ቁጥር 165 ታኅሣሥ 23 2014



