በቀጣዩ ሳምንት 400 ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል ይመጣሉ ሲሉ ኔታናሁ ገለጹ

Views: 151

 

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ 400 ኢትዮጵያውያን (ቤተ እስራኤላውያን) ወደ እስራኤል እንደሚገቡ መወሰኑን በማስታወስ፣ በቀጣዩ ሳምንትም ወደ እስራኤል ይመጣሉ ሲሉ ተናገሩ።

ወደ እስራኤል የሚሄዱት ዜጎች ቤተሰቦቻቸው እስራኤል ወስጥ እንደሚኖሩ የተነገረ ሲሆን፣ በቀጣዩ ሳምንት የመጀመሪያው አውሮፕላን 400 ዜጎችን አሳፍሮ ወደ እስራኤል እንደሚያቀና ተስፋ አለኝ ሲሉም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታናሁ ተናግረዋል።

ወደ እስራኤል የሚሄዱት ቤተ እስራኤላውን በፈረንጆቹ ግንቦት 2 ላይ የሚደረገው ምርጫ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎም ይጠበቃል ሲል ‹ታይምስ ኦፎ እስራኤል› የሂብሪው ሚዲያን በምንጭነት ጠቀሶ ዘግቧል። ዜጎቹም ሲገቡ ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኙ አስፈላጊ ምርመራዎችና ሌሎች ሥራዎችም እንደሚሠራ ተጠቁሟል።

በአሁን ወቅት በእስራኤል 140 ሺሕ ቤተ እስራኤለውን እንደሚገኙም ዘገባው አስታውሷል።

 

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com