ጨፌው ‹‹ገዳ የኢኮኖሚ ልዩ ዞን›› ለመመስረት የቀረበ አዋጅን  አጸደቀ

Views: 354

ጨፌው ‹‹ገዳ የኢኮኖሚ ልዩ ዞን›› ለመመስረት የቀረበ አዋጅን  አጸደቀ

 

ጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ የካቲት 11/2012 በነበረው ውሎ ‹‹ገዳ የኢኮኖሚ ልዩ ዞን›› ለመመስረት የቀረበ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አጸደቀ።

ገዳ የኢኮኖሚ ልዩ ዞን በምሥራቅ ሸዋ ዞን በሉሜ ወረዳ 13 ቀበሌዎችን እና በአዳማ ከተማ ኹለት ቀበሌዎችን ያቀፈ ሲሆን፥ 24 ሺሕ ሄክታር መሬት እንደሚሸፍን ተነግሯል።

ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ሥራው ሲጠናቀቅ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የተገለጸ ሲሆን፣

የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ግብርና ማቀነባበሪያ፣ የሳይንስ ቴክኖሎጂ ፓርኮች፣ ቢሮዎችና የሠራተኞች መኖሪያን ያካተተ እንደሆነም ተጠቀሷል።

እንዲሁም ለኅብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ ትምህርት ቤት፣ የጤናና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ያካትታል፡፡ የኢኮኖሚ ዞኑም  በቦርድ የሚተዳደር ይሆናል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ጨፌው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የረቂቅ ሕግ አዘገጃጀት ሥርዓትን ለመወሰን የወጣ አዋጅን ተወያይቶ ማጽደቁን የኦሮሚያ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

 

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com