የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) የትይዩ ካቢኔ አዋቅሮ ወደ ሥራ አስገባ

0
291

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የመንግሥትን ሥራ የሚከታተል ትይዩ ያለዉን ካቢኔ መመሥረቱን አስታወቀ።
ካቢኔው ከመንግሥት ትይዩ የዕለት ተዕለት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ሥራ ከመከታተል፣ የፖሊሲ ንድፈ ሐሳቦችን እስከ መቅረጽ ኃላፊነት እንደተጣለበት ፓርቲው ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
ፓርቲው 22 አባላት ያሉት ትይዩ ካቢኔ መመሥረቱ ከምርጫ ሰሞን እንቅስቃሴ ባሻገር፣ የዕለት-ተዕለት መንግሥታዊ ሥራዎችን ለመከታተል እና በቀጣይ ለማሟያ ምርጫ ራሱን ለማዘጋጀት እንደሚያግዘው ፓርቲው አሳውቋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 166 ታኅሣሥ 30 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here