አርብ ጥር 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በትናንትናው ዕለት በቻይና በተካሄደና በቀጥታ ስርጭት በተላለፈ ሁነት ላይ በ5 ሴኮንዶች ውስጥ 11 ሺህ ከረጢት የኢትዮጵያ ቡና መሸጡ ተገልጿል፡፡
በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በተሳተፉበት በዚህ ሁነት ላይ ወደ ቻይና የሚላከው የኢትዮጵያ ቡና መጠን ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ196 በመቶ መጨመሩም ተነግሯል፡፡
በጥቅሉ ወደ ቻይና የሚላኩ የአፍሪካ የግብርና ምርቶች መጠንም በመጪዎቹ ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




