የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የዲጂታል ትምህርት ፕላትፎርም ማልማቱን አስታወቀ፡፡
በኤግልላየንስ ሲስትም ቴክኖሎጂ በተበለጸገው ስኩል ኦፍ ክላውድ የተሰኘ የሞባይል እና የድህረ ገጽ መተግበሪያ ዙሪያ ሥራ ፈጣሪው ኤርሚያስ አመልጋ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የታወቀ ሲሆን፣ በቀጣይ ሳምንትም መተግበሪያው በይፋ እንደሚመረቅ ታውቋል።
በቀጣይ ሳምንት የሚመረቀው “ስኩል ኦፍ ክላውድ” የተሰኘ የሞባይል እና የድህረ ገጽ መተግበሪያ በትምህርት ጥራት ጉድልት እና የመምሀራን ብቃት ማነስ ምክንያት የተፈጠረውን የትምህርት ጥራት ጉድለት በቴክኖጂ ለመቅረፍ ያለመ እና በኢትዮጱያ የመጀመሪያ የሆነ የዲጂታል ትምህርት ቤት ለመመስረት መሆኑ ታውቋል።
ኤርሚያስ አመልጋ በዚሁ ስኩል ኦፍ ክላውድ ፕሮጀክት አንዱ ምእራፍ በሆነው ማስትር ክላስ ድርሻ ይዘው በተለያዩ መስኮች በተለይም በንግድ ክህሎት፣ በስራ ፈጠራ እና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ተሞከሮ እውቅት በመትግብሪያው አማካኝነት ትምህርት እና ሰልጥና የሚሰጡበት እንድሚሆን ማረጋገጥ ተችሏል።
የማስተር ክላስ ሃስብ በዋነኝነት ሙያዊ፣ ሰነ ልቦናዊ እንዲሁም የአመራር ከህሎታቸውን ለማዳበር ያለመ መሆኑን የኤግልላየን መስራች እና ስራ አስፈጻሚ በእርሱፍቃድ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ያሉ ከኹለት ሚሊዮን በላይ የኤርሚያስ አመልጋ ተከታይ እና አድናቂዎች የስልጠናው ተጠቃሚ እንድሚሆኑ እና በመተግበሪያው የተለያዩ ትጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በቀጣይም ይካተቱበታል ተብሏል።
ማስተር ክላስ በሰለጠነው ምዕራባውያን አለም የተለመደ እና ሚሊዮን ዶላሮች የሚንቀሳቀሱበት ፕላትፎርም ሲሆን፣ በዓለም ላይ በተለያዩ መስኮች ለውጥ ያመጡ እና ተጻእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ለአድናቂ እና ትከታዮቻችው የህይወት ክህሎት ስልጠና የሚሰጡበት ነው።
ባለሀብቱ የሚሰጡትን ትምህርት በማስተር ካርድ ቪዛ እና ሌሎች የውጪ እና የአገር ውስጥ ዲጂታል የክፍያ መንገዶች በመጠቀም በየትኛውም አገራት የሚገኙ ማስተር ክላሱን መከታተል የሚፈልጉ ሰዎች ከሶስት እስከ አምስት ዶላር ወይንም በ100 ብር ክፍያ መተግበሪያውን በመጠቀም መከታተል እንድሚችሉ የኤግልላየን መስራች እና ስራ አስፈጻሚ በእርሱፍቃድ ጌታቸው ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ኤርሚያስ አመልጋ በበኩሊ በቀጣይ ሳመንት በመተግበሪያው የሚለቀቁ ስልጠናዎች በተለይም ለወጣቱ አዉንታዊ ተጻእኖ ለመፍጠር የሚያስችል እንደሚሆን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
በስኩል ኦፍ ክላውድ መተግብሪያ አማካኝነት የስራ ፈጠራ፣ የንግድ ክህሎት፣ የስብእና ግንባታ፣ የጤና አጠባበቅ፣ የአመራር ክህሎትን ማሳድግ የሚያስቻል ስልጠና እንድሚሰጡበት ገልጸው ከንግድ እና ሰራ ፈጠራ በተጨማሪ፣ በጤና አጠባበቅ፣ በአመራር ጥበብ፣ በስነ ህይወት፣ በካፒታል ማርኬት እንዲሁም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሁኔታ በጥልቅ ትንታኔ የሚያካትት ስልጠና እንደሚሰጡ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
በሱፈቃድ ጌታቸው በበኩላቸው ስኩል ኦፍ ክላውድ በትመህርት ቤቶች በተለይም በግል እና በመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም በከተማ እና ገጠር ተማሪዎች መካከል ያለውን የትምህርት አሰጣጥ እና በተማሪዎች አቀባበል መሀል ያለውን ሰፊ ከፍተት መሙላተ የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
“ስኩል ኦፍ ክላውድ” በዲጂታል የመማር ማስተማር ዘዴ የትምህርት ጥራትን የሚያሻሸል እንድሚሆን በእርሱፈፍቃድ ተናግረዋል።
የዲጂታል ትምህርት መተግበሪያው ከመጀምሪያ ደረጃ ጀመሮ እስከ ኹለተኛ ደረጃ እንደሚዘልቅ ሲሆን፣ ሁሉንም የትምሀርት አይነቶች በምስል እና ትርካ መልክ የያዘ በመሆኑ የተማሪዎችን የመርዳት እና የማስታወስ አቅም እንድሚጨምር ገልጽው በተለየ መልኩ ኢትዮጲያዊነት መገለጫ የሆኑ የግብርገብ ትምህርት ያካተተ መትግብሪያ ነው ተብሏል፡፡
በአለም ግዙፍ ከሆነው የቻይና የኤሌክትሮኒክ ገበያ አሊባባ ኩባንያ ወደ አገር ገብቶ በስድስት ወራት ውስጥ ሰራ እንደሚጀምር የተሰማ ሲሆን፣ ከኤግልላየንስ ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በአሊባባ የኤሌክትሮኒክ መገበያያ ወደ ሰራ ሲገባ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ እና ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አብረው ለማከናውን ቅድመ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኤርሚያስ ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።
በቀጣይም ወራት ከአሊባባ ኩባንያ ተውካዮች ወደ አገር ቤት እንደሚመጡ እና የገበያ ጥናት እና የመጋዘኖች መጠን እንዲሁም አድራሻዎች መረጣ እንድሚያካሂዱ አስረድተዋል። የአሊባባ ኤሌክትሮኒክ መገበያያ በኤርሚያስ አመልጋ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ውስጥ ስራ እንድሚጀምር የታወቀ ሲሆን፣ በዚህም ከመላው የአፍሪካ አገራት መገበያያት የሚያስችል ከመሆኑ በተጨማሪ በቀጠናዊ ንግድ ትስስር አማካኝነት ወደ አገር ውስጥ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ማስገባት የሚያስችል መሆኑን በተለይ ለአዲስ ማለዳ ገልጸውዋል።
ከ20 ዓመታት በላይ የአሜሪካ ቆየታ በኋላ 1988 ወደ ኢትዮጵያ የተመልሱት ኤርሚያስ አመልጋ የተከያዩ የንግድ ተቋማትን መመስረታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ቅጽ 4 ቁጥር 168 ጥር 14 2014


