በሱማሌ ክልል ፋፋን እና ሲቲ ዞኖች ከፍተኛ ምርት መታጣቱ ተገለጸ

0
1245

ከእነዚህም መካከል እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የማሽላ እና የበቆሎ ምርት፣ ከተጠበቀው የስንዴ ምርት 30 በመቶ እንዲሁም ከታሰበው የሽንኩርት እና የቲማቲም ምርት 30 በመቶው ታጥቷል። በተመሳሳይ በደቡብ ኦሮሚያ 70 በመቶ ምርት እንደታጣም ተገልጿል።
በደቡብ ኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች በእንስሳት መኖ እና ውኃ ዕጥረት ቢያንስ 267 ሺሕ ከብቶች መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በተጨማሪም በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ለአደጋ ተጋልጠዋል ተብሏል። ከብቶቹ አስቸኳይ መኖ፣ ውኃ እና ክትባትም ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት በሱማሌ 2.3 ሚሊዮን፣ ከ870,000 በላይ ደግሞ በደቡብ ኦሮሚያ በአጠቃላይ ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለውኃ ዕጥረት መጋለጣቸውን ‹ኦቻ› በሪፖርቱ አስፍሯል።
በአጠቃላይ፣ በኹሉም ድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ከ6.4 ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም ኦቻ አስታውቋል።
ከእነዚህም መካከል በሱማሌ ክልል 3 ሚሊዮን፣ በምሥራቅ ኦሮሚያ 2.4 ሚሊዮን እና በደቡብ ኦሮሚያ 1 ሚሊዮን ዜጎች ይገኙበታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 168 ጥር 14 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here