አርብ ጥር 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት ሐሙስ እንዳስታወቀው ዋሽንግተን የሚገኘዉ የአሜሪካ መንግሥት በሱዳን የሚታየዉ ቀዉስ እስካላበቃ እና በሲቪል የሚመራ መንግስት ወደ ስልጣን እስካልተመለሰ ድረስ ለአገሪቱ የመደበውን የኢኮኖሚ ድጋፍ እንደማይቀጥል ገልጿል።
በመግለጫዉ መሰረት እንደ አንድ የዓለም አቀፍ የቅጣት እርምጃዎች አካል፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ጥቅምት ወር ላይ ከተካሄደዉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በኋላ ለሱዳን መድባዉ የነበረዉን 700 ሚሊዮን ዶላር ወይም (623 ሚሊዮን- ይሮ) የአደጋ ጊዜ ርዳታ አቋርጣለች ሲል ዶይቸ ቬለ ዘግቧል።
_______________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



