ሰብዓዊ አቅርቦትን አራግፈው እየተመለሱ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ እንዲመለሱ መገደዳቸው ተገለፀ

0
756

የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው “ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ ነበር” ተብሎ የተነገሯቸው 27 የጭነት መኪኖች ወደ መቀሌ እንዳይገቡ ተደርገዋል ብለዋል

ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሽብርተኝት የተፈረጀው የህመሃት ቡድን በአፋር ክልል በአዲስ መልክ ጥቃት እየፈጸመ በመሆኑ ሰብዓዊ አቅርቦትን ትግራይ ክልል አድርሰው ሲመለሱ የነበሩ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች እንዳይወጡ መታገዳቸው ተገልጿል።

ቡድኑ ተሽከርካሪዎቹን ከግማሽ መንገድ በኋላ ወደ መቀሌ እንዲመለሱ ማስገደዱን በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ቡድኑ በአፋር እንደ አዲስ በጀመረው ወረራና ጭፍጨፋ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች መፈናቀላቸውንም የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

የህወሃት ቡድን መሪዎች ሕዝቡን በማስራብ ለፖለቲካ አጀንዳቸው በግልጽ ሲጠቀሙበት እየተስተዋለ መሆኑንም መረጃው ጠቁሟል፡፡

ቡድኑ ከዚህ ቀደምም ሰብዓዊ አቅርቦትን ጭነው ወደ ትግራይ የገቡ 1 ሺህ 10 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች እርዳታውን አራግፈው እንዳይመለሱ በማድረግ፣ ለታጣቂዎቹና ከአማራና አፋር ለዘረፋቸው ንብረቶች ማመላለሻነት ሲጠቀም መቆየቱ ይታወሳል።

በዚህ ሂደት ግን የተሽከርካሪዎቹ ባለቤት የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራምም ይሁን ሰብዓዊነት ያሳስበናል በሚል ኢትዮጵያ ላይ የወመቱ መንግሥታትና ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ድምፃቸውን አጥፍተዋል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ ማምሻውን ለዶቼቬሌ በሰጡት ቃል ህወሓት ጥቃት የከፈተዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በሌለበት ሁኔታ ነው ብለዋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ሲል በትዊተር ገፃቸው ላይ የጻፉት የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው “ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ ነበር” ተብሎ የተነገሯቸው ሰብአዊ ዕርዳታ የጫኑ የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም 27 የጭነት መኪኖች ወደ መቀሌ እንዳይገቡ ተደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here